“እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ በእኔ የሚያምን እኔ የምሠራውን ሥራ እርሱም ይሠራል፤ ከዚያም የሚበልጥ ይሠራል፤ እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና።
ሐዋርያት ሥራ 19:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ ታላላቅ ሥራን ይሠራ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ እጅግ የሚያስደንቅ ታምራትን ያደርግ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በጣም አስደናቂ የሆኑ ተአምራትን በጳውሎስ እጅ ያደርግ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር፤ ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር፥ |
“እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ በእኔ የሚያምን እኔ የምሠራውን ሥራ እርሱም ይሠራል፤ ከዚያም የሚበልጥ ይሠራል፤ እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና።
በጌታም ፊት ደፍረው እያስተማሩ፥ እርሱም የጸጋውን ቃል ምስክር እያሳየላቸው፥ በእጃቸውም ድንቅ ሥራና ተአምራትን እያደረገላቸው ብዙ ወራት ኖሩ።
ያንጊዜም ሕዝቡ ሁሉ ጸጥ ብለው እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያደረገላቸውን ተአምራትና ድንቅ ሥራ ሁሉ ሲናገሩ ጳውሎስንና በርናባስን አዳመጡአቸው።
ብዙ ቀንም እንዲሁ ታደርግ ነበር፤ ጳውሎስንም አሳዘነችው፤ መለስ ብሎም፥ “መንፈስ ርኩስ፥ ከእርስዋ እንድትወጣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝዤሃለሁ” አለው፤ ወዲያውኑም ተዋት።
በሐዋርያት እጅም በሕዝቡ ዘንድ ተአምራትና ድንቅ ሥራዎች ይሠሩ ነበር፤ በቤተ መቅደስም በሰሎሞን መመላለሻ በአንድነት ነበሩ።
ሲሞንም ወዲያውኑ አምኖ ተጠመቀ፤ ፊልጶስንም ይከተል ጀመር፤ በፊልጶስም እጅ የሚደረገውን ተአምርና ታላቅ ኀይል ባየ ጊዜ ይደነቅ ነበር።
እርሱ መንፈስ ቅዱስን የሚሰጣችሁ፥ ኀይልንም የሚያደርግላችሁ የኦሪትን ሥራ በመሥራት ነውን? ወይስ ሃይማኖትን በመስማት ነው?
እግዚአብሔርም እንደ ራሱ ፈቃድ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ በመስጠት፥ በምልክትና በድንቅ ነገር፥ በልዩ ልዩ ተአምራትም መሰከረላቸው፤ ነገራቸውንም አስረዳላቸው።