በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፤ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም።
ሐዋርያት ሥራ 17:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያንጊዜም ወንድሞች ጳውሎስን ሸኝተው ወደ ባሕር አደረሱት፤ ሲላስና ጢሞቴዎስ ግን በዚያው ቀሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ወንድሞች ጳውሎስን ቶሎ ብለው ወደ ባሕሩ ዳርቻ ሰደዱት፤ ሲላስና ጢሞቴዎስ ግን እዚያው ቀሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜም ወንድሞች ወዲያው ጳውሎስን እስከ ባሕር ድረስ ይሄድ ዘንድ ሰደዱት፤ ሲላስና ጢሞቴዎስም በዚያው ቀሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ ወንድሞች በቶሎ ጳውሎስ ወደ ባሕሩ አጠገብ እንዲሄድ አደረጉት፤ ሲላስና ጢሞቴዎስ ግን እዚያው በቤርያ ቀሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜም ወንድሞቹ ወዲያው ጳውሎስን እስከ ባሕር ድረስ ይሄድ ዘንድ ሰደዱት፤ ሲላስና ጢሞቴዎስም በዚያው ቀሩ። |
በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፤ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም።
ከዚህም በኋላ ሐዋርያትና ቀሳውስት ሕዝቡም ሁሉ ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ የሚልኳቸውን ሰዎች ይመርጡ ዘንድ ተስማሙ፤ ከባልንጀሮቻቸው መካከልም የተማሩትን ሰዎች በርናባስ የተባለ ይሁዳንና ሲላስን መረጡ።
ወደ ደርቤንና ወደ ልስጥራን ከተማም ደረሰ፤ እነሆም፥ በዚያ የአንዲት ያመነች አይሁዳዊት ልጅ ጢሞቴዎስ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበር፤ አባቱ ግን አረማዊ ነበረ።
ጳውሎስን የሸኙት ሰዎችም እስከ አቴና ከተማ ድረስ አብረውት መጥተው ነበርና ፈጥነው ይከተሉት ዘንድ ወደ ሲላስና ወደ ጢሞቴዎስ ላካቸው፤ ተመልሰውም ሄዱ።
ከእነርሱና ከደጋጎች አረማውያንም ብዙ ሰዎች፥ ከታላላቆች ሴቶችም ጥቂቶች ያይደሉ አምነው ከጳውሎስና ከሲላስ ጋር ሆኑ።
በአጧቸውም ጊዜ ኢያሶንን ጐተቱት፤ በዚያም የነበሩትን ጓደኞች ጭምር ወደ ሹሞቹ ወሰዱአቸው፤ እየጮኹም እንዲህ ይሉ ነበር፥ “ዓለምን የሚያውኳት እነዚህ ናቸው፤ ወደዚህም መጥተዋል።
ሲላስና ጢሞቴዎስም ከመቄዶንያ በወረዱ ጊዜ ጳውሎስ፥ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ለአይሁድ እየመሰከረ ቃሉን በማስተማር ይተጋ ነበር።
ከሚያገለግሉትም ሁለቱን ጢሞቴዎስንና አርስጦስን ወደ መቄዶንያ ላከ፤ እርሱ ራሱ ጳውሎስ ግን ብዙ ቀን በእስያ ተቀመጠ።
በዚያም ሦስት ወር ተቀመጠ፤ ወደ ሶርያም በመርከብ ለመሄድ ዐስቦ ሳለ አይሁድ ስለ ተማከሩበት ወደ መቄዶንያ ሊመለስ ቈረጠ።
ወደ መቄዶንያ በሄድሁ ጊዜ፥ አንዳንዶች ልዩ ትምህርትን እንዳያስተምሩና ወደ ተረት መጨረሻም ወደሌለው ወደ ትውልዶች ታሪክ እንዳያደምጡ ልታዛቸው በኤፌሶን ትቀመጥ ዘንድ ለመንሁህ፤ እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮች ክርክርን ያመጣሉና፤ በእምነት ግን ላለ ለእግዚአብሔር መጋቢነት አይጠቅሙም።
እርስዋም፥ “የሚከተሉአችሁ እንዳያገኙአችሁ ወደ ተራራው ሂዱ፤ የሚከተሉአችሁም እስከሚመለሱ ድረስ በዚያ ሦስት ቀን ተሰውራችሁ ተቀመጡ፤ በኋላም መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ” አለቻቸው።