Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ጢሞቴዎስ 1:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3-4 ወደ መቄዶንያ በሄድሁ ጊዜ፥ አንዳንዶች ልዩ ትምህርትን እንዳያስተምሩና ወደ ተረት መጨረሻም ወደሌለው ወደ ትውልዶች ታሪክ እንዳያደምጡ ልታዛቸው በኤፌሶን ትቀመጥ ዘንድ ለመንሁህ፤ እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮች ክርክርን ያመጣሉና፤ በእምነት ግን ላለ ለእግዚአብሔር መጋቢነት አይጠቅሙም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ወደ መቄዶንያ በሄድሁ ጊዜ ዐደራ እንዳልሁህ፣ አንዳንድ ሰዎች ከእንግዲህ የሐሰት ትምህርት እንዳያስተምሩ ታዝዛቸው ዘንድ በዚያው በኤፌሶን ተቀመጥ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ወደ መቄዶንያ በምሄድ ጊዜ በኤፌሶን ተቀምጠህ አንዳንድ ሰዎች ልዩ ትምህርትን እንዳያስተምሩ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ወደ መቄዶንያ ስሄድ ሳለሁ ዐደራ እንዳልኩህ እዚያ ያሉ አንዳንድ ሰዎች የሐሰት ትምህርት እንዳያስተምሩ ታደርጋቸው ዘንድ በኤፌሶን ተቀመጥ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3-4 ወደ መቄዶንያ በሄድሁ ጊዜ፥ አንዳንዶች ልዩ ትምህርትን እንዳያስተምሩና ወደ ተረት መጨረሻም ወደሌለው ወደ ትውልዶች ታሪክ እንዳያደምጡ ልታዛቸው በኤፌሶን ትቀመጥ ዘንድ ለመንሁህ፤ እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮች ክርክርን ያመጣሉና በእምነት ግን ላለ ለእግዚአብሔር መጋቢነት አይጠቅሙም።

Ver Capítulo Copiar




1 ጢሞቴዎስ 1:3
24 Referencias Cruzadas  

ወደ ኤፌ​ሶ​ንም ደረሱ፤ በዚ​ያም ተዋ​ቸ​ውና እርሱ ብቻ​ውን ወደ ምኵ​ራብ ገብቶ አይ​ሁ​ድን ተከ​ራ​ከ​ራ​ቸው።


ከዚ​ህም በኋላ በሚ​ሸ​ኙት ጊዜ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቢፈ​ቅድ እን​ደ​ገና እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ አሁን ግን የሚ​መ​ጣ​ውን በዓል በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላደ​ርግ እወ​ዳ​ለሁ” አላ​ቸው፤ ከኤ​ፌ​ሶ​ንም በመ​ር​ከብ ሄደ።


መቄ​ዶ​ን​ያና አካ​ይያ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቅዱ​ሳን መካ​ከል ላሉ ድሆች አስ​ተ​ዋ​ጽ​ፅኦ ለማ​ድ​ረግ ተባ​ብ​ረ​ዋ​ልና።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እና​ንተ የተ​ማ​ራ​ች​ሁ​ትን ትም​ህ​ርት የሚ​ቃ​ወ​ሙ​ትን፥ መለ​ያ​የ​ት​ንና ማሰ​ና​ከ​ያን የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን እን​ድ​ታ​ው​ቁ​ባ​ቸው እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ተለዩ፤


ወደ እና​ንተ የመ​ጣና እኛ ወደ አላ​ስ​ተ​ማ​ር​ና​ችሁ ወደ ሌላ ኢየ​ሱስ የጠ​ራ​ችሁ ቢኖር፥ ወይም ያል​ተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁት ሌላ መን​ፈስ ቢኖር፥ ወይም ያል​ተ​ማ​ራ​ች​ሁት ሌላ ወን​ጌል ቢኖር ልት​ጠ​ብ​ቁን ይገ​ባል።


እን​ግ​ዲህ በሽ​ን​ገ​ላ​ቸው ያስቱ ዘንድ በሚ​ተ​ና​ኰሉ ሰዎች ተን​ኰል ምክ​ን​ያት በት​ም​ህ​ርት ነፋስ ሁሉ ወዲ​ያና ወዲህ እየ​ተ​ፍ​ገ​መ​ገ​ም​ንና እየ​ተ​ን​ሳ​ፈ​ፍን ሕፃ​ናት አን​ሁን።


እኔም ፈጥኜ እን​ደ​ም​መጣ በጌ​ታ​ችን አም​ና​ለሁ።


ይህን እዘዝና አስተምር። በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ፥ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው።


ስለዚህ ወንድሞችን ብታሳስብ፥ በእምነትና በተከተልኸው በመልካም ትምህርት ቃል የምትመገብ የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም አገልጋይ ትሆናለህ።


ያለ ነቀፋ እንዲሆኑ ይህን ደግሞ እዘዝ።


ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፤ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።


በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ፥ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።


እነዚህን አስተምርና ምከር። ማንም ልዩ ትምህርት የሚያስተምር ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ጤናማ ቃልና እግዚአብሔርን ለመምሰል በሚስማማ ትምህርት የማይጠጋ ቢሆን፥


በዚያን ቀን ከጌታ ምሕረትን እንዲያገኝ ጌታ ይስጠው፤ በኤፌሶንም እንዴት እንዳገለገለኝ አንተ በደኅና ታውቃለህ።


ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ገብተዋልና፤ እነርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ናቸው፤ ይህ አሳቹና የክርስቶስ ተቃዋሚው ነው።


ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ።


ዳሩ ግን ‘ነቢይ ነኝ’ የምትለውን ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos