ሐዋርያት ሥራ 11:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ‘አቤቱ፥ ከቶ አይሆንም፤ ንጹሕ ያልሆነ ርኩስ ነገር ወደ አፌ ገብቶ አያውቅም’ አልሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኔም፣ ‘ጌታ ሆይ! ይህማ አይሆንም፤ ርኩስ ወይም ያልተቀደሰ ነገር ፈጽሞ ወደ አፌ ገብቶ አያውቅም’ አልሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ‘ጌታ ሆይ! አይሆንም፤ ርኩስ ወይም የሚያስጸይፍ ከቶ ወደ አፌ ገብቶ አያውቅምና፤’ አልሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ግን ‘አይሆንም ጌታ ሆይ! ንጹሕ ያልሆነ ወይም ርኩስ ነገር በአፌ ገብቶ አያውቅም’ አልኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም፦ “ጌታ ሆይ፥ አይሆንም፤ ርኵስ ወይም የሚያስጸይፍ ከቶ ወደ አፌ ገብቶ አያውቅምና” አልሁ። |
በራሱ ርኩስ የሆነ ነገር እንደሌለ በጌታችን በኢየሱስ ሆኜ ዐውቄአለሁ፤ ተረድቼአለሁም፤ ነገር ግን ማናቸውም ነገር ርኩስ እንደሚሆን ለሚያስብ ያ ለእርሱ ርኩስ ነው።
የማያምን ባል በሚስቱ ይቀደሳልና፤ የማታምን ሚስትም በባልዋ ትቀደሳለችና፤ ያለዚያማ ልጆቻቸው ርኩሳን ይሆናሉ፤ አሁን ግን ቅዱሳን ናቸው።