በዙሪያቸውም ያሉ ሁሉ በፈቃዳቸው ካቀረቡት ሁሉ ሌላ በብር ዕቃና በወርቅ፥ በገንዘቦችና በእንስሶች፥ በሌላም ስጦታ ይረዷቸው ነበር።
2 ጢሞቴዎስ 2:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በትልቅም ቤት የእንጨትና የሸክላ ዕቃ ደግሞ አለ እንጂ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ አይደለም፤ እኵሌቶቹም ለክብር፥ እኵሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአንድ ትልቅ ቤት ውስጥ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ ሳይሆን፣ የዕንጨትና የሸክላ ዕቃም ይኖራል፤ ከእነዚህ አንዳንዶቹ ለከበረ፣ ሌሎቹም ለተራ አገልግሎት ይውላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአንድ ትልቅ ቤት ውስጥ የወርቅና የብር ዕቃዎች ብቻ ሳይሆኑ የእንጨትና የሸክላ ዕቃዎችም ደግሞ ይኖራሉ፤ እኩሌቶቹም ለክብር፥ እኩሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በትልቅ ቤት ውስጥ ከወርቅና ከብር የተሠሩ ዕቃዎች ብቻ ሳይሆኑ ከእንጨትና ከሸክላ የተሠሩ ዕቃዎችም ይገኛሉ፤ ከእነርሱም አንዳንዶቹ ለተከበረ አገልግሎት፥ አንዳንዶቹም ክብር ለሌለው አገልግሎት ይውላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በትልቅም ቤት የእንጨትና የሸክላ ዕቃ ደግሞ አለ እንጂ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ አይደለም፥ እኵሌቶቹም ለክብር፥ እኵሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፤ |
በዙሪያቸውም ያሉ ሁሉ በፈቃዳቸው ካቀረቡት ሁሉ ሌላ በብር ዕቃና በወርቅ፥ በገንዘቦችና በእንስሶች፥ በሌላም ስጦታ ይረዷቸው ነበር።
ናቡከደነዖርም በኢየሩሳሌም ካለው መቅደስ ወስዶ ወደ ባቢሎን ያመጣው የእግዚአብሔር ቤት የወርቅና የብር ዕቃ ይሰጥ፤ በኢየሩሳሌምም ወዳለው መቅደስ ወደ ስፍራው ይወሰድ፤ በእግዚአብሔርም ቤት ይኑር።
ለመሠዊያው ክዳን ሥራለት፤ መሸፈኛውን፥ ጽዋዎቹን፥ የሥጋ ሜንጦዎቹን፥ የእሳት መጫሪያዎቹንም አድርግ። ዕቃውንም ሁሉ ከናስ አድርግ።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እኔ አባቴን አከብራለሁ እንጂ ጋኔን የለብኝም፤ እናንተ ግን ትንቁኛላችሁ።
በእግዚአብሔር ሥራ እንተባበራለንና፤ የእግዚአብሔርም አገልጋዮች ነንና፤ እናንተም የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ።
ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።
እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።