Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ጢሞቴዎስ 2:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 በትልቅ ቤት ውስጥ ከወርቅና ከብር የተሠሩ ዕቃዎች ብቻ ሳይሆኑ ከእንጨትና ከሸክላ የተሠሩ ዕቃዎችም ይገኛሉ፤ ከእነርሱም አንዳንዶቹ ለተከበረ አገልግሎት፥ አንዳንዶቹም ክብር ለሌለው አገልግሎት ይውላሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በአንድ ትልቅ ቤት ውስጥ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ ሳይሆን፣ የዕንጨትና የሸክላ ዕቃም ይኖራል፤ ከእነዚህ አንዳንዶቹ ለከበረ፣ ሌሎቹም ለተራ አገልግሎት ይውላሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 በአንድ ትልቅ ቤት ውስጥ የወርቅና የብር ዕቃዎች ብቻ ሳይሆኑ የእንጨትና የሸክላ ዕቃዎችም ደግሞ ይኖራሉ፤ እኩሌቶቹም ለክብር፥ እኩሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 በትልቅም ቤት የእንጨትና የሸክላ ዕቃ ደግሞ አለ እንጂ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ አይደለም፤ እኵሌቶቹም ለክብር፥ እኵሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 በትልቅም ቤት የእንጨትና የሸክላ ዕቃ ደግሞ አለ እንጂ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ አይደለም፥ እኵሌቶቹም ለክብር፥ እኵሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፤

Ver Capítulo Copiar




2 ጢሞቴዎስ 2:20
15 Referencias Cruzadas  

ጐረቤቶቻቸውም ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ዕቃዎችን፥ ቈሳቊሶችንና ከብቶችን፥ ሌሎችንም ጠቃሚ የሆኑ ስጦታዎችና በቤተ መቅደስ መባ ሆኖ የሚቀርብ ሌላም ነገር በመለገሥ ረዱአቸው።


እንዲሁም ከዚህ በፊት ንጉሥ ናቡከደነፆር በኢየሩሳሌም ከነበረው ቤተ መቅደስ ማርኮ ያወጣቸው ከወርቅና ከብር የተሠሩትም ንዋያተ ቅድሳት ወደዚያው ተመልሰው በኢየሩሳሌም በሚሠራው ቤተ መቅደስ በተገቢ ቦታቸው ይቀመጡ።”


ዐመድ የሚጠራቀምባቸውን ድስቶችን፥ የእሳት መጫሪያዎችን፥ ጐድጓዳ ሳሕኖችን፥ ሜንጦዎችንና ማንደጃዎችን አዘጋጅ፤ ሁሉም ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ።


የከበሩ የጽዮን ልጆች እንደ ንጹሕ ወርቅ ያኽል ውድ ነበሩ፤ እንዴት አሁን የሸክላ ሠሪ እጅ እንደ ሠራው እንደ ሸክላ ዕቃ ተቈጠሩ!


የወይን ጠጅ እየጠጡ ሳለ ብልጣሶር ሞቅ ባለው ጊዜ አባቱ ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ያመጣቸውን ከወርቅና ከብር የተሠሩ ጽዋዎችን እንዲያመጡ አገልጋዮቹን አዘዘ፤ ንጉሡ ይህን ያደረገው እርሱና መኳንንቱ፥ ሚስቶቹና ቁባቶቹ በእነዚያ የወርቅ ጽዋዎች እንዲጠጡባቸው ፈልጎ ነው።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እኔ ጋኔን የለብኝም፤ ነገር ግን አባቴን አከብራለሁ፤ እናንተ ግን ታዋርዱኛላችሁ።


አንተ ሰው! ከእግዚአብሔር ጋር ለመከራከር ምን መብት አለህ? የሸክላ ዕቃ ሠሪውን “ለምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ?” ሊለው ይችላልን?


እኛ ለእግዚአብሔር አብረን የምንሠራ አገልጋዮች ነን፤ እናንተም የእግዚአብሔር እርሻና የእግዚአብሔር ሕንጻ ናችሁ።


ነገር ግን ይህ ከሁሉ የሚበልጠው ኀይል የእግዚአብሔር እንጂ የእኛ አለመሆኑ እንዲታወቅ ይህን ክቡር ነገር እንደ ሸክላ ዕቃ ሆነን ይዘነዋል።


እግዚአብሔር በመንፈሱ የሚያድርበት ሕንጻ ለመሆን እናንተም አብራችሁ በክርስቶስ ትታነጻላችሁ።


ወደ ጌታ ኢየሱስ የምትቀርቡትም እንደ ሕያዋን ድንጋዮች መንፈሳዊ ቤት ሆናችሁ ለመታነጽ ነው፤ በዚህ ዐይነት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ቅዱሳን ካህናት ትሆናላችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos