2 ተሰሎንቄ 1:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ በምትታገሱበት በስደታችሁና በመከራችሁ ሁሉ ከመጽናታችሁና ከእምነታችሁ የተነሣ በእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት ስለ እናንተ ራሳችን እንመካለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በደረሰባችሁ ስደትና መከራ ሁሉ በመጽናታችሁ፣ እኛ ራሳችን ስለ ትዕግሥታችሁና ስለ እምነታችሁ በእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ እንመካለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ በምትታገሱት መከራችሁና በስደታችሁ ሁሉ ስለ እናንተ መጽናትና እምነት እኛ ራሳችን በእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት በእናንተ እንመካለን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ምንም እንኳ ብዙ ችግርና ሥቃይ ቢደርስባችሁ እናንተ እንዴት ታጋሾችና በእምነታችሁ የጸናችሁ መሆናችሁን በመናገር እኛ በሌሎች አብያተ ክርስቲያን መካከል ሆነን በእናንተ እንመካለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ በምትታገሱበት በስደታችሁና በመከራችሁ ሁሉ ከመጽናታችሁና ከእምነታችሁ የተነሣ በእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት ስለ እናንተ ራሳችን እንመካለን። |
በበጎ ምግባር ጸንተው ለሚታገሡ፥ ምስጋናና ክብርን፥ የማይጠፋ ሕይወትንም ለሚሹ እርሱ የዘለዓለም ሕይወትን ይሰጣቸዋል።
ነገር ግን ሁሉ እግዚአብሔር እንደ አደለው፥ ሁሉም እግዚአብሔር እንደ ጠራው እንዲሁ ይኑር፤ ለአብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ እንዲህ ሥርዐት እንሠራለን።
ስለዚህም ስለ ክርስቶስ መከራ መቀበልን፥ መሰደብን፥ መጨነቅን፥ መሰደድን፥ መቸገርንም ወደድሁ፤ መከራ በተቀበልሁ ጊዜ ወዲያውኑ እበረታለሁና።
ስለ እናንተ ለእርሱ በተመካሁበት ሁሉ አላሳፈራችሁኝምና፤ ነገር ግን ሁሉን ለእናንተ በእውነት እንደ ተናገርን፥ እንደዚሁ ደግሞ በቲቶ ፊት ትምክህታችን እውነት ሆነ።
በእናንተ ዘንድ እንዲሁ ብዙ መወደድ አለኝ፤ ስለ እናንተም የምመካበት ብዙ ነው፤ መጽናናትንም አገኘሁ፤ ከመከራዬም ሁሉ ይልቅ ደስታዬ በዛልኝ።
እናንተ እንደምትተጉ አውቃለሁና፤ ስለዚህም “የአካይያ ሰዎች እኮ ከአምና ጀምሮ አዘጋጅተዋል” ብዬ በመቄዶንያ ሰዎች ዘንድ አመሰገንኋችሁ፤ እነሆም የእናንተ መፎካከር ብዙዎችን ሰዎች አትግቶአቸዋል።
ምናልባት የመቄዶንያ ሰዎች ከእኔ ጋር ቢመጡና ሳታዘጋጁ ቢያገኙአችሁ እናንተ ታፍራላችሁ ባልልም እኛ ስለ እናንተ ከነገርናቸው የተነሣ እናፍራለን።
እናንተ ወንድሞች ሆይ! በይሁዳ የሚኖሩትን በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉትን የእግዚአብሔርን ማኅበሮች የምትመስሉ ሆናችኋልና፤ እነርሱ ከአይሁድ መከራ እንደ ተቀበሉ፥ እናንተ ደግሞ ያንን መከራ ከአገራችሁ ሰዎች ተቀብላችኋልና።
እነሆ በትዕግሥት የጸኑትን ብፁዓን እንላቸዋለን፤ ኢዮብ እንደ ታገሠ ሰምታችኋል፤ ጌታም እንደ ፈጸመለት አይታችኋል፤ ጌታ እጅግ የሚምር የሚራራም ነውና።