Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ተሰሎንቄ 2:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ተስፋችን ወይስ ደስታችን ወይስ የትምክህታችን አክሊል ማን ነው? በጌታችን በኢየሱስ ፊት በመምጣቱ እናንተ አይደላችሁምን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ጌታችን ኢየሱስ ሲመጣ በርሱ ፊት ተስፋችን ወይም ደስታችን ወይም አክሊላችን ማን ነው? እናንተ አይደላችሁምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ጌታችን ኢየሱስ በሚመጣበት ጊዜ በፊቱ የተስፋችን ወይም የደስታችን ወይም የመመክያችን አክሊል ምንድነው? እናንተ አይደላችሁምን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ታዲያ፥ ተስፋችን ወይም ደስታችን ወይም ጌታችን ኢየሱስ በሚመጣበት ጊዜ በፊቱ የምንመካበት የድል አክሊላችን እናንተ አይደላችሁምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ተስፋችን ወይስ ደስታችን ወይስ የትምክህታችን አክሊል ማን ነው? በጌታችን በኢየሱስ ፊት በመምጣቱ እናንተ አይደላችሁምን?

Ver Capítulo Copiar




1 ተሰሎንቄ 2:19
35 Referencias Cruzadas  

ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት፤ ክፉ ሴት ግን ነቀዝ እንጨትን እንደሚበላ እንዲዚሁ ባሏን ትጐዳለች።


የእውነት ከንፈር በንጉሥ ዘንድ የተወደደ ነው፥ ቅን ነገርንም ይወድዳል።


የሽማግሌዎች አክሊል የልጅ ልጆች ናቸው፤ የልጆችም ክብር አባቶቻቸው ናቸው።


ለራስህ የሞገስ አክሊልን ትሰጥሃለች፥ በደስታ አክሊልም ትጠብቅሃለች።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ያማረ አክ​ሊል፥ በአ​ም​ላ​ክ​ሽም እጅ የመ​ን​ግ​ሥት ዘውድ ትሆ​ኛ​ለሽ።


የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል።


በዚህም በዘማዊና በኀጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በአባቱ ክብር ከቅዱሳን መላእክት ጋር በመጣ ጊዜ በእርሱ ያፍርበታል።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እስ​ክ​መጣ ይኖር ዘንድ ብወ​ድ​ድስ አን​ተን ምን አግ​ዶህ፤ አንተ ግን ተከ​ተ​ለኝ” አለው።


ነገር ግን ሰው ሁሉ በየ​ሥ​ር​ዐቱ ይነ​ሣል፤ በመ​ጀ​መ​ሪያ ከሙ​ታን የተ​ነሣ ክር​ስ​ቶስ ነው፤ ከዚያ በኋላ በክ​ር​ስ​ቶስ ያመኑ እርሱ በሚ​መ​ጣ​በት ጊዜ ይነ​ሣሉ።


ጊዜው ሳይ​ደ​ርስ ዛሬ ለምን ትመ​ረ​ም​ራ​ላ​ቸሁ? በጨ​ለማ ውስጥ የተ​ሰ​ወ​ረ​ው​ንም የሚ​ያ​በራ፥ የል​ብን አሳ​ብም የሚ​ገ​ልጥ ጌታ​ችን ይመ​ጣል፤ ያን​ጊዜ ሁሉም ዋጋ​ውን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይቀ​በ​ላል።


እኛ መመ​ኪ​ያ​ችሁ እን​ደ​ሆን፥ እን​ዲሁ እና​ን​ተም በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ቀን መመ​ኪ​ያ​ችን እን​ድ​ት​ሆኑ በከ​ፊል እን​ዳ​ወ​ቃ​ችሁ ተስፋ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።


የሕ​ይ​ወ​ትን ቃል እያ​ስ​ተ​ማ​ራ​ችሁ፤ ክር​ስ​ቶስ በሚ​መ​ጣ​በት ቀን እኔ እን​ድ​መካ፤ የሮ​ጥሁ በከ​ንቱ አይ​ደ​ለ​ምና፤ የደ​ከ​ም​ሁም በከ​ንቱ አይ​ደ​ለ​ምና።


አሁ​ንም የተ​ወ​ደ​ዳ​ች​ሁና የም​ና​ፍ​ቃ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ደስ​ታ​ች​ንና አክ​ሊ​ላ​ችን ናችሁ፤ ወዳ​ጆ​ቻ​ችን ሆይ፥ እን​ዲህ ቁሙ፤ በጌ​ታ​ች​ንም ጽኑ።


እናንተ ክብራችን ደስታችንም ናችሁና።


በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና፤ እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉቱን አንቀድምም፤


የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።


ስለዚህ በምትታገሱበት በስደታችሁና በመከራችሁ ሁሉ ከመጽናታችሁና ከእምነታችሁ የተነሣ በእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት ስለ እናንተ ራሳችን እንመካለን።


ነገር ግን ወንድሞች ሆይ! ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣትና ወደ እርሱ ስለ መሰብሰባችን፥ በመንፈስ ወይም በቃል ወይም ከእኛ እንደሚመጣ በመልእክት “የጌታ ቀን ደርሶአል፤” ብላችሁ ከአእምሮአችሁ ቶሎ እንዳትናወጡ እንዳትደነግጡም እንለምናችኋለን።


እንግዲህ ወንድሞች ሆይ! ጌታ እስኪመጣ ድረስ ታገሡ። እነሆ ገበሬው የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እስኪቀበል ድረስ እርሱን እየታገሠ የከበረውን የመሬት ፍሬ ይጠብቃል።


እናንተ ደግሞ ታገሡ፤ ልባችሁንም አጽኑ፤ የጌታ መምጣት ቀርቦአልና።


የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ።


የእርሱን ግርማ አይተን እንጂ በብልሃት የተፈጠረውን ተረት ሳንከተል የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ኀይልና መምጣት አስታወቅናችሁ።


እነርሱም “የመምጣቱ የተስፋ ቃል ወዴት ነው? አባቶች ከሞቱባት ጊዜ ከፍጥረት መጀመሪያ ይዞ ሁሉ እንዳለ ይኖራልና፤” ይላሉ።


አሁንም፥ ልጆች ሆይ፥ በሚገለጥበት ጊዜ እምነት እንዲሆንልን በመምጣቱም በእርሱ ፊት እንዳናፍር በእርሱ ኑሩ።


ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው፤


እነሆ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዐይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፤ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፤ አሜን።


“እነሆ በቶሎ እመጣለሁ፤ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos