ከመላው ነገደ እስራኤል የተሰበሰቡ ሕዝብ፥ “ንጉሡ ዳዊት ከጠላቶቻችን እጅ ታድጎናል፥ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ አድኖናል፤ አሁንም ስለ አቤሴሎም ከሀገሩና ከመንግሥቱ ሸሸ።
2 ሳሙኤል 8:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን መታ፤ አዋረዳቸውም፤ ዳዊትም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ምርኮን ወሰደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን ድል አደረጋቸው፤ በቍጥጥሩም ሥር አዋላቸው፤ ሜቴግ አማ የተባለችውንም ከተማ ከፍልስጥኤማውያን ቍጥጥር ነጻ አደረጋት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን ድል አደረጋቸው፤ በቁጥጥሩም ሥር አደረጋቸው፥ ሜተግ አማ የተባለችውንም ከተማ ዳዊት ከፍልስጥኤማውያን እጅ ወሰደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥቂት ዘግየት ብሎም ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን ድል አድርጎ በቊጥጥሩ ሥር አደረጋቸው፤ “ሜቴግ አማ” የተባለችውንም ከተማ ከእነርሱ እጅ ወሰደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን መታ፥ አዋረዳቸውም፥ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ሜቴግ አማ የተባለችውን ከተማ ወሰደ። |
ከመላው ነገደ እስራኤል የተሰበሰቡ ሕዝብ፥ “ንጉሡ ዳዊት ከጠላቶቻችን እጅ ታድጎናል፥ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ አድኖናል፤ አሁንም ስለ አቤሴሎም ከሀገሩና ከመንግሥቱ ሸሸ።
ኢዮአብና አቢሳም አበኔርን አሳደዱ፤ ፀሐይም ጠለቀች፤ እነርሱም በገባዖን ምድረ በዳ መንገድ በጋይ ፊት ለፊት እስካለው እስከ አማን ኮረብታ ድረስ መጡ።
ፍልስጥኤማውያንም ዳዊት በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ እንደ ተቀባ ሰሙ፤ ፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ዳዊትን ሊፈልጉ ወጡ፤ ዳዊትም በሰማ ጊዜ ወደ ምሽጉ ወረደ።
በሄድህበትም ሁሉ ከአንተ ጋር ነበርሁ፤ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋሁ፤ በምድርም ላይ እንዳሉ እንደ ታላላቆቹ ስም ስምህን ታላቅ አደረግሁ።
እነርሱ በእምነት ተጋደሉ፤ ነገሥታትን ድል ነሡ፤ ጽድቅን አደረጉ፤ ተስፋቸውን አገኙ፤ የአናብስትንም አፍ ዘጉ ።
የእሳት ኀይልን አጠፉ፤ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፤ ከድካማቸው በረቱ፤ በጦርነት ኀይለኞች ሆኑ፤ የባዕድ ጭፍሮችንም አባረሩ።
እግዚአብሔርም ፍልስጥኤማውያንን አዋረዳቸው፤ ዳግመኛም ከዚያ ወዲያ ወደ እስራኤል ድንበር አልወጡም፤ በሳሙኤልም ዘመን ሁሉ የእግዚአብሔር እጅ በፍልስጥኤማውያን ላይ ነበረች።