Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ሳሙኤል 22:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 ከአ​ሕ​ዛብ ጠብ አድ​ነኝ፤ የአ​ሕ​ዛ​ብም ራስ አድ​ር​ገህ ትሾ​መ​ኛ​ለህ፤ የማ​ላ​ው​ቀው ሕዝብ ተገ​ዛ​ልኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 “በሕዝቤ ከተቃጣብኝ አደጋ አዳንኸኝ፤ የመንግሥታትም ራስ አደረግኸኝ። የማላውቀውም ሕዝብ ተገዛልኝ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 ከሕዝቤ ጥቃት አዳንከኝ፤ የመንግሥታትም ራስ አደረግኸኝ፤ የማላውቀው ሕዝብ ተገዛልኝ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 ከዐመፀኛ ሕዝብ አዳንከኝ፤ በአሕዛብም ላይ ሾምከኝ፤ የማላውቀውም ሕዝብ ይገዛልኛል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 ከሕዝብ ክርክር ታድነኛለህ፥ የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ፥ የማላውቀው ሕዝብም ይገዛልኛል።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 22:44
26 Referencias Cruzadas  

እነሆ፥ የማ​ያ​ው​ቁህ ሕዝብ ይጠ​ሩ​ሃል፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ አክ​ብ​ሮ​ሃ​ልና ስለ አም​ላ​ክህ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የማ​ያ​ው​ቁህ ሕዝብ በአ​ንተ ይማ​ጠ​ናሉ።


በሳ​ኦል ቤትና በዳ​ዊት ቤት መካ​ከል ለብዙ ጊዜ ጦር​ነት ሆነ፤ የዳ​ዊት ቤት እየ​በ​ረታ፥ የሳ​ኦል ቤት ግን እየ​ደ​ከመ የሚ​ሄድ ሆነ።


የይ​ሁ​ዳ​ንም ሰዎች ሁሉ ልብ እንደ አንድ ሰው ልብ አድ​ርጎ አዘ​ነ​በለ፤ ወደ ንጉ​ሡም፥ “አን​ተና ብላ​ቴ​ኖ​ችህ፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህም ሁሉ ተመ​ለሱ” ብለው ላኩ​በት።


ከመ​ላው ነገደ እስ​ራ​ኤል የተ​ሰ​በ​ሰቡ ሕዝብ፥ “ንጉሡ ዳዊት ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን እጅ ታድ​ጎ​ናል፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም እጅ አድ​ኖ​ናል፤ አሁ​ንም ስለ አቤ​ሴ​ሎም ከሀ​ገ​ሩና ከመ​ን​ግ​ሥቱ ሸሸ።


ዛሬም ያዘ​ዝ​ሁ​ህን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ሰም​ተህ ብት​ጠ​ብ​ቃት፥ ብታ​ደ​ር​ጋ​ትም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራስ ያደ​ር​ግ​ሃል እንጂ ጅራት አያ​ደ​ር​ግ​ህም፤ ሁል​ጊ​ዜም በላይ እንጂ በታች አት​ሆ​ንም።


ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም “የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል፤”


ኢሳ​ይ​ያ​ስም ደግሞ እን​ዲህ ብሎ​አል፥ “የእ​ሴይ ዘር ይነ​ሣል፤ ከእ​ርሱ የሚ​ነ​ሣ​ውም ለአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ ይሆ​ናል፤ ሕዝ​ቡም ተስፋ ያደ​ር​ጉ​ታል።”


ነቢዩ ሆሴዕ እን​ዲህ እን​ዳለ “ወገኔ ያል​ነ​በ​ረ​ውን ወገኔ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ወዳጄ ያል​ነ​በ​ረ​ች​ው​ንም ወዳጄ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ።


በም​ድ​ርም ላይ ለእኔ እዘ​ራ​ታ​ለሁ፤ ይቅ​ርታ የሌ​ላ​ትን ይቅር እላ​ታ​ለሁ፤ ያል​ተ​ወ​ደ​ደች የነ​በ​ረ​ች​ውን እወ​ድ​ዳ​ታ​ለሁ፤ ሕዝ​ቤም ያል​ሆ​ነ​ውን፥ “አንተ ሕዝቤ ነህ” እለ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም፥ “አንተ ጌታ​ዬና አም​ላኬ ነህ” ይለ​ኛል።


ያል​ፈ​ለ​ጉኝ አገ​ኙኝ፤ ላል​ጠ​የ​ቁ​ኝም ተገ​ኘሁ፤ ስሜን ላል​ጠራ ሕዝብ፥ “እነ​ሆኝ” አል​ሁት።


ለአ​ን​ቺም የማ​ይ​ገዙ ነገ​ሥ​ታት ይሞ​ታሉ፤ እነ​ዚ​ያም አሕ​ዛብ ፈጽ​መው ይጠ​ፋሉ።


የአ​ሕ​ዛ​ብን ርስት ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ለሕ​ዝቡ የሥ​ራ​ውን ብር​ታት አሳየ።


ለም​ነኝ፥ አሕ​ዛ​ብን ለር​ስ​ትህ የም​ድ​ር​ንም ዳርቻ፥ ለግ​ዛ​ትህ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።


ያቺም ሴት ወደ ሕዝቡ ሁሉ ገብታ ለከ​ተ​ማው ሕዝብ ሁሉ በብ​ል​ሀት ነገ​ረ​ቻ​ቸው፤ የቢ​ኮ​ሪን ልጅ የሳ​ቡ​ሄን ራስ ቈር​ጠው ሰጡ​አት፤ ወደ ኢዮ​አ​ብም ጣለ​ችው። ኢዮ​አ​ብም መለ​ከ​ቱን ነፋ፤ ሰውም ሁሉ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ርቆ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ድን​ኳኑ ሄደ። ኢዮ​አ​ብም ወደ ንጉሡ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሰ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገድ ሁሉ ወደ ኬብ​ሮን ወደ ዳዊት መጥ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “እኛ የአ​ጥ​ን​ትህ ፍላጭ የሥ​ጋህ ቍራጭ ነን።


እነሆ፥ ለአ​ሕ​ዛብ ምስ​ክር፥ ለወ​ገ​ኖ​ችም አለ​ቃና አዛዥ እን​ዲ​ሆን አደ​ረ​ግ​ሁት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios