La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 7:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ናታ​ንም ንጉ​ሡን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና፥ ሂድና በል​ብህ ያሰ​ብ​ኸ​ውን ሁሉ አድ​ርግ” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ናታንም፣ ንጉሡን “እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ ስለ ሆነ፣ ያሰብኸውን ሁሉ አድርግ” ሲል መለሰለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ናታንም፥ “ጌታ ካንተ ጋር ስለሆነ፥ በልብህ ያለውን ሁሉ አድርግ” አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ናታንም “እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስለ ሆነ በልብህ ያሰብከውን ሁሉ አድርግ” ሲል መለሰለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ናታንም ንጉሡን፦ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ሂድ፥ በልብህም ያለውን ሁሉ አድርግ አለው።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 7:3
14 Referencias Cruzadas  

በዚ​ያም ሌሊት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ናታን መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለው፦


ነገር ግን ካህኑ ሳዶ​ቅና የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ ነቢ​ዩም ናታን፥ ሳሚም፥ ሬሲም፥ የዳ​ዊ​ትም ኀያ​ላን አዶ​ን​ያ​ስን አል​ተ​ከ​ተ​ሉም ነበር።


ወደ ተራ​ራ​ውም ወደ ኤል​ሳዕ ደርሳ እግ​ሮ​ቹን ጨበ​ጠች፤ ግያ​ዝም ሊያ​ር​ቃት መጣ፤ ኤል​ሳ​ዕም፥ “ነፍ​ስዋ አዝ​ና​ለ​ችና ተዋት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያን ከእኔ ሰው​ሮ​ታል፤ አል​ነ​ገ​ረ​ኝ​ምም” አለ።


ዳዊ​ትም ሰሎ​ሞ​ንን እን​ዲህ አለው፥ “ልጄ ሆይ፥ እኔ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት እሠራ ዘንድ በልቤ አስቤ ነበር።


ንጉ​ሡም ዳዊት በጉ​ባ​ኤው መካ​ከል ቆሞ እን​ዲህ አለ፥ “ወን​ድ​ሞቼና ሕዝቤ ሆይ፥ ስሙኝ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለቃል ኪዳኑ ታቦ​ትና ለአ​ም​ላ​ካ​ችን እግር ማረ​ፊያ የዕ​ረ​ፍት ቤት ለመ​ሥ​ራት አሳብ በልቤ መጣ​ብኝ፤ ለዚ​ህም ሥራ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ውን አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ፤


የን​ጉ​ሡም የዳ​ዊት የፊ​ተ​ኛ​ውና የኋ​ለ​ኛው ነገር፥ እነሆ፥ በባ​ለ​ራ​እዩ በሳ​ሙ​ኤል ታሪክ፥ በነ​ቢ​ዩም በና​ታን ታሪክ፥ በባለ ራእ​ዩም በጋድ ታሪክ ተጽ​ፎ​አል።


ይህ​ንም ትእ​ዛዝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በነ​ቢ​ያቱ እጅ አዝ​ዞ​አ​ልና እንደ ዳዊ​ትና እንደ ንጉሡ ባለ ራእይ እንደ ጋድ፥ እንደ ነቢ​ዩም እንደ ናታን ትእ​ዛዝ፥ ጸና​ጽ​ልና በገና፥ መሰ​ን​ቆም አስ​ይዞ ሌዋ​ው​ያ​ንን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቆመ።


ሕይ​ወ​ትን ለመ​ነህ፥ ሰጠ​ኸ​ውም፥ ለረ​ዥም ዘመን ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ።


ኀጢ​አቴ ከራሴ ጠጕር በዝ​ቷ​ልና፥ እንደ ከባድ ሸክ​ምም በላዬ ከብ​ዶ​አ​ልና።


እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ።


እነ​ዚ​ህም ምል​ክ​ቶች በደ​ረ​ሱህ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና እጅህ የም​ት​ች​ለ​ውን ሁሉ አድ​ርግ።


ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም፥ “ልብህ ያሰ​ኘ​ህን ሁሉ አድ​ርግ እነሆ፥ ከአ​ንተ ጋር ነኝ፤ እንደ አንተ ልብ የእ​ኔም ልብ እን​ዲሁ ነው” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ፊቱን፥ የቁ​መ​ቱ​ንም ዘለ​ግታ አትይ፤ ሰው እን​ደ​ሚ​ያይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አያ​ይ​ምና ናቅ​ሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ልብን ያያል” አለው።