Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ሳሙኤል 14:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም፥ “ልብህ ያሰ​ኘ​ህን ሁሉ አድ​ርግ እነሆ፥ ከአ​ንተ ጋር ነኝ፤ እንደ አንተ ልብ የእ​ኔም ልብ እን​ዲሁ ነው” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ወጣቱም ጋሻ ጃግሬ፣ “በልብህ ያሰብኸውን ሁሉ አድርግ፤ ወደ ኋላም አትበል፤ እኔም በሙሉ ልብ ካንተው ጋራ ነኝ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ወጣቱ ጋሻ ጃግሬም፥ “በልብህ ያሰብኸውን ሁሉ አድርግ፤ ወደ ኋላም አትበል፤ እኔም በሙሉ ልብ ካንተው ጋር ነኝ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ወጣቱም ጋሻጃግሬ “የምትፈቅደውን ነገር ሁሉ አድርግ፤ እኔ ከአንተ አልለይም፤ በሙሉ ልቤም ከአንተ ጋር ነኝ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ጋሻ ጃግሬውም፦ ልብህ ያሰኘህን ሁሉ አድርግ፥ እነሆ፥ ከአንተ ጋር ነኝ፥ እንደ አንተ ልብ ሁሉ የእኔም ልብ እንዲሁ ነው አለው።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 14:7
8 Referencias Cruzadas  

የን​ጉ​ሡም ብላ​ቴ​ኖች ንጉ​ሡን፥ “እነሆ፥ ጌታ​ችን ንጉሥ የመ​ረ​ጠ​ውን ሁሉ እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አሉት።


ናታ​ንም ንጉ​ሡን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና፥ ሂድና በል​ብህ ያሰ​ብ​ኸ​ውን ሁሉ አድ​ርግ” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለም​ድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤ በማ​ስ​ተ​ዋል ዘምሩ፤


የሠራዊትም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ዘመን ከአሕዛብ ቋንቋ ሁሉ አሥር ሰዎች የአንዱን አይሁዳዊ ሰው ልብስ ዘርፍ ይዘው፦ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና ከእናንተ ጋር እንሂድ ይላሉ።


እር​ሱም ፈጥኖ ጋሻ ዣግ​ሬ​ውን ጠርቶ፥ “ሴት ገደ​ለ​ችው እን​ዳ​ይሉ ሰይ​ፍ​ህን መዝ​ዘህ ግደ​ለኝ” አለው፤ ጐል​ማ​ሳ​ውም ወጋው፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክም ሞተ።


እነ​ዚ​ህም ምል​ክ​ቶች በደ​ረ​ሱህ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና እጅህ የም​ት​ች​ለ​ውን ሁሉ አድ​ርግ።


ዮና​ታ​ንም ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን፥ “ና፥ ወደ እነ​ዚህ ቈላ​ፋን ሰፈር እን​ለፍ፤ በብዙ ወይም በጥ​ቂት ማዳን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አያ​ስ​ቸ​ግ​ረ​ው​ምና ምና​ል​ባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይረ​ዳን ይሆ​ናል” አለው።


ዮና​ታ​ንም አለው፥ “እነሆ፥ ወደ ሰዎቹ እና​ል​ፋ​ለን፤ ወደ እነ​ር​ሱም እን​ቀ​ር​ባ​ለን፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos