2 ሳሙኤል 3:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ኢዮአብንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሕዝብ ሁሉ፥ “ልብሳችሁን ቅደዱ፤ ማቅም ልበሱ፤ በአበኔርም ፊት አልቅሱ” አላቸው። ንጉሡም ዳዊት ከቃሬዛው በኋላ ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዳዊት ለኢዮአብና ዐብሮት ለነበረው ሕዝብ ሁሉ፣ “ልብሳችሁን ቀድዳችሁ፣ ማቅ ለብሳችሁ በአበኔር ፊት አልቅሱ” አላቸው፤ ራሱ ንጉሥ ዳዊትም አስከሬኑን አጀበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ዳዊት ለኢዮአብና አብሮት ለነበረው ሕዝብ ሁሉ፥ “ልብሳችሁን ቀዳችሁና ማቅ ለብሳችሁ በአበኔር ፊት አልቅሱ” አላቸው፤ ንጉሡም ዳዊት ከቃሬዛው በኋላ ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ዳዊት በሐዘን ልብሳቸውን ቀደው፥ ማቅ ለብሰው ለአበኔር እንዲያለቅሱ ኢዮአብንና የእርሱ ተከታዮች የሆኑትን ሰዎች አዘዘ፤ በቀብር ሥነ ሥርዓቱም ላይ ንጉሥ ዳዊት ራሱ አስክሬኑን ተከትሎ ሄደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ኢዮአብንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሕዝብ ሁሉ፦ ልብሳችሁን ቅደዱ፥ ማቅም ልበሱ፥ በአበኔርም ፊት አልቅሱ አላቸው። ንጉሡም ዳዊት ከቃሬዛው በኋላ ሄደ። |
በሦስተኛውም ቀን፥ እነሆ፥ ከሰፈር ከሳኦል ወገን አንድ ሰው ልብሱን ቀድዶ፥ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ መጣ፤ ወደ ዳዊትም በመጣ ጊዜ በምድር ላይ ወድቆ ሰገደለት።
የእስራኤልም ልጆች ተቈጠሩ፤ ሊገጥሙአቸውም ወጡ፤ የእስራኤልም ልጆች እንደ ሁለት ትናንሽ የፍየል መንጋዎች ሆነው በፊታቸው ሰፈሩ፤ ሶርያውያን ግን ምድርን ሞልተዋት ነበር።
የቤቱንም አዛዥ ኤልያቄምን ጸሓፊውንም ሳምናስን የካህናቱንም አለቆች ማቅ ለብሰው ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ ይሄዱ ዘንድ ላካቸው።
ኢያሱም ልብሱን ቀደደ፤ እርሱና የእስራኤልም ሽማግሌዎች በእግዚአብሔር ታቦት ፊት እስከ ማታ ድረስ በግንባራቸው ተደፉ፤ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ።
እርስዋንም ባየ ጊዜ ልብሱን ቀድዶ፥ “ወዮልኝ ልጄ ሆይ! ወደ እግዚአብሔር አፌን ከፍቻለሁና፥ ከዚያውም እመለስ ዘንድ አልችልምና አሰናከልሽኝ፤ አስጨነቅሽኝም” አላት።