Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ሳሙኤል 3:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 አበ​ኔ​ር​ንም በኬ​ብ​ሮን ቀበ​ሩት፤ ንጉ​ሡም ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ በመ​ቃ​ብሩ አጠ​ገብ አለ​ቀሰ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ለአ​በ​ኔር አለ​ቀ​ሱ​ለት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ከዚያም አበኔርን በኬብሮን ቀበሩት፤ ንጉሡም በአበኔር መቃብር ላይ ጮኾ አለቀሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ እንደዚሁ አለቀሱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 አበኔርንም በኬብሮን ቀበሩት፤ ንጉሡም ጮኾ በአበኔር መቃብር ላይ አለቀሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ እንደዚሁ አለቀሱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 አበኔር በኬብሮን ተቀበረ፤ በመቃብሩም ላይ ንጉሡ ድምፁን ከፍ አድርጎ አለቀሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ እርሱን በማየት በመረረ ሁኔታ አለቀሱ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 አበኔርንም በኬብሮን ቀበሩት፥ ንጉሡም ድምፁን ከፍ አድርጎ በአበኔር መቃብር አጠገብ አለቀሰ፥ ሕዝቡም ሁሉ አለቀሱ። ንጉሡም ለአበኔር፦

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 3:32
8 Referencias Cruzadas  

ጠላትህ ቢወድቅ ደስ አይበልህ፥ በመሰናከሉም አትታበይ።


በል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በዋ​ሸሁ ነበ​ርና ይህ ደግሞ ትልቅ በደል ይሁ​ን​ብኝ።


ንጉ​ሡም እጅግ ደነ​ገጠ፤ በበ​ሩም ላይ ወዳ​ለ​ችው ሰገ​ነት ወጥቶ አለ​ቀሰ፤ ሲሄ​ድም፥ “ልጄ አቤ​ሴ​ሎም ሆይ፥ ልጄ፥ ልጄ አቤ​ሴ​ሎም ሆይ፥ በአ​ንተ ፋንታ እኔ እን​ድ​ሞት ቤዛ​ህም እን​ድ​ሆን ማን ባደ​ረ​ገኝ፥ ልጄ አቤ​ሴ​ሎም፥ ልጄ ሆይ፥” ይል ነበር።


በጦር ወድ​ቀ​ዋ​ልና ለሳ​ኦ​ልና ለልጁ ለዮ​ና​ታን፥ ለይ​ሁ​ዳም ሕዝብ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ወገን እንባ እያ​ፈ​ሰሱ አለ​ቀሱ፤ እስከ ማታም ድረስ ጾሙ።


ዳዊ​ትና ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሕዝብ ድም​ፃ​ቸ​ውን ከፍ አድ​ር​ገው ለማ​ል​ቀስ ኀይል እስ​ኪ​ያጡ ድረስ አለ​ቀሱ።


ዳዊ​ትም ጐል​ማ​ሶ​ቹን አዘዘ፤ ገደ​ሉ​አ​ቸ​ውም፤ እጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ቈር​ጠው በኬ​ብ​ሮን በውኃ መቆ​ሚያ አጠ​ገብ አን​ጠ​ለ​ጠ​ሉ​አ​ቸው። የኢ​ያ​ቡ​ስ​ቴን ራስ ግን ወስ​ደው በአ​በ​ኔር መቃ​ብር በኬ​ብ​ሮን ቀበ​ሩት።


በጠ​ላቴ ውድ​ቀት ደስ ብሎኝ እንደ ሆነ፥ በል​ቤም እሰይ ብዬ እንደ ሆነ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios