ዮሴፍም አላቸው፥ “ይህን አደርግ ዘንድ አይገባኝም፤ ጽዋው የተገኘበት ሰው እርሱ አገልጋይ ይሁነኝ እንጂ፤ እናንተ ግን ወደ አባታችሁ በደኅና ሂዱ።”
2 ሳሙኤል 23:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አቤቱ፥ ይህን አደርግ ዘንድ ከእኔ ይራቅ፤ ነፍሳቸውን ሰጥተው የሄዱ ሰዎች ደም አይደለምን?” ብሎ ይጠጣ ዘንድ አልወደደም። ሦስቱ ኀያላንም ያደረጉት ይህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እርሱም፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲህ ያለውን ነገር ላደርግ? ይህስ ከእኔ ይራቅ! ይህ በነፍሳቸው ቈርጠው የሄዱ ሰዎች ደም አይደለምን?” አለ፤ ዳዊትም ሊጠጣው አልፈለገም። እንግዲህ ሦስቱ ኀያላን ሰዎች ያደረጉት ጀብዱ እንዲህ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እርሱም፥ ጌታ ሆይ፤ እንዲህ ያለውን ነገር ላደርግ? ይህስ ከእኔ ይራቅ! ይህ በነፍሳቸው ቆርጠው የሄዱ ሰዎች ደም አይደለምን?” ብሎ፥ ዳዊት ሊጠጣው አልፈለገም። ሦስቱ ኀያላን ሰዎች የፈጸሙአቸው ተግባሮች እነዚህ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር ሆይ! ይህን ውሃ ከቶ ልጠጣው አልችልም! እኔ እርሱን ብጠጣ፥ በነፍሳቸው ቈርጠው የሄዱትን የእነዚህን ኀያላን ሰዎች ደም እንደ ጠጣሁ ይቈጠራል!” አለ፤ ውሃውንም መጠጣት እምቢ አለ። ዝነኞች የሆኑት ሦስቱ ኀያላን ወታደሮች የፈጸሙአቸው የጀግንነት ተግባሮች እነዚህ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ ይህን አደርግ ዘንድ ከእኔ ይራቅ፥ በነፍሳቸው ደፍረው የሄዱ ሰዎች ደም አይደለምን? ብሎ ይጠጣ ዘንድ አልወደደም። ሦስቱ ኃያላን ያደረጉት ይህ ነው። |
ዮሴፍም አላቸው፥ “ይህን አደርግ ዘንድ አይገባኝም፤ ጽዋው የተገኘበት ሰው እርሱ አገልጋይ ይሁነኝ እንጂ፤ እናንተ ግን ወደ አባታችሁ በደኅና ሂዱ።”
“ይህን አደርግ ዘንድ አምላኬ ሆይ፥ ለእኔ አይገባኝም፤ ሰውነታቸውንም ለሞት አሳልፈው አምጥተውታልና የእነዚህን ሰዎች ደም እጠጣለሁን?” አለ። ስለዚህም ዳዊት ይጠጣው ዘንድ አልወደደም። ሦስቱም ኀያላን ያደረጉት ይህ ነው።
“ከእስራኤልም ልጆች፥ ወይም በመካከላቸው ከሚኖሩ እንግዶች ማናቸውም ሰው ደም ቢበላ፥ ደም በሚበላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብድበታለሁ፤ ያንም ሰው ከሕዝቡ ለይች አጠፋዋለሁ።
ስለዚህም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእውነት ቤትህ፥ የአባትህም ቤት፤ ለዘለዓለም በፊቴ እንዲኖር ተናግሬአለሁ፤ አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ አይሆንልኝም።
እግዚአብሔርም በቀባው ላይ እጄን እዘረጋ ዘንድ እግዚአብሔር ከእኔ ያርቀው፤ አሁንም በራሱ አጠገብ ያለውን ጦርና የውኃውን መንቀል ይዘህ እንሂድ፤” አለው።