Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ሳሙኤል 23:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የሶ​ር​ህ​ያም ልጅ የኢ​ዮ​አብ ወን​ድም አቢሳ የሦ​ስቱ አለቃ ነበር። እር​ሱም ጦሩን በሦ​ስቱ መቶ ላይ አን​ሥቶ ገደ​ላ​ቸው፤ ስሙም በሦ​ስቱ ዘንድ ተጠ​ርቶ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ ኀያላን አለቃ ነበረ። በሦስት መቶ ሰዎች ላይ ጦሩን ሰብቆ የገደላቸውና እንደ ሦስቱ ኀያላን ሁሉ እርሱም ዝናን ያተረፈ ሰው ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ ኀያላን አለቃ ነበረ። በሦስት መቶ ሰዎች ላይ ጦሩን ሰብቆ የገደላቸውና ስሙም ከሦስቱ ኀያላን ጋር የሚጠራ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የጽሩያም ልጅ የኢዮአብ ወንድም አቢሳ ዝነኞች የሆኑት የሠላሳዎቹ ወታደሮች አለቃ ነበር፤ እርሱም ጦሩን አንሥቶ ከሦስት መቶ ሰዎች ጋር በመዋጋት ሁሉንም ገደለ፤ ስለዚህም እንደ ሦስቱ ዝነኛ ሆነ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የጽሩያም ልጅ የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሠላሳው አለቃ ነበረ። እርሱም ጦሩን በሦስቱ መቶ ላይ አንሥቶ ገደላቸው፥ ስሙም እንደ ሦስቱ ተጠርቶ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 23:18
11 Referencias Cruzadas  

የአ​ሞን ልጆ​ችም ሶር​ያ​ው​ያን እንደ ሸሹ ባዩ ጊዜ እነ​ርሱ ደግሞ ከአ​ቢሳ ፊት ሸሹ፤ ወደ ከተ​ማ​ዪ​ቱም ገቡ፤ ኢዮ​አ​ብም ከአ​ሞን ልጆች ዘንድ ተመ​ልሶ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ገባ።


የቀ​ረ​ው​ንም ሕዝብ ከወ​ን​ድሙ ከአ​ቢሳ ጋር ላከ፤ በአ​ሞን ልጆች ፊትም አሰ​ለ​ፋ​ቸው።


ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡን ከኢ​ዮ​አብ እጅ በታች ሢሶ​ውን፥ ከኢ​ዮ​አ​ብም ወን​ድም ከሶ​ር​ህያ ልጅ ከአ​ቢሳ እጅ በታች ሢሶ​ውን፥ ከጌት ሰውም ከኤቲ እጅ በታች ሢሶ​ውን ላከ። ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡን፥ “እኔ ደግሞ ከእ​ና​ንተ ጋር እወ​ጣ​ለሁ” አላ​ቸው።


እኅ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሶር​ህ​ያና አቢ​ግያ ነበሩ። የሶ​ር​ህ​ያም ልጆች አቢሳ፥ ኢዮ​አብ፥ አሣ​ሄል እኒህ ሦስቱ ነበሩ።


አሜ​ሳይ ግን በኢ​ዮ​አብ እጅ ከነ​በ​ረው ሰይፍ አል​ተ​ጠ​ነ​ቀ​ቀም ነበር፤ ኢዮ​አ​ብም ሆዱን ወጋው፤ አን​ጀ​ቱ​ንም በም​ድር ላይ ዘረ​ገ​ፈው፤ ሁለ​ተ​ኛም አል​ወ​ጋ​ውም፤ ሞተም። ኢዮ​አ​ብና ወን​ድሙ አቢ​ሳም የቢ​ኮ​ሪን ልጅ ሳቡ​ሄን አሳ​ደዱ።


ኢዮ​አ​ብና ወን​ድሙ አቢ​ሳም በሰ​ልፍ በገ​ባ​ዖን ወን​ድ​ማ​ቸ​ውን አሣ​ሄ​ልን ገድሎ ነበ​ርና አበ​ኔ​ርን ይገ​ድ​ሉት ዘንድ ይጠ​ባ​በቁ ነበር።


በዚ​ያም ሦስቱ የሦ​ር​ህያ ልጆች ኢዮ​አ​ብና አቢሳ፥ አሣ​ሄ​ልም ነበሩ፤ የአ​ሣ​ሄ​ልም እግ​ሮቹ ፈጣ​ኖች ነበሩ፤ እንደ ዱር ሚዳ​ቋም ሯጭ ነበረ።


እር​ሱም ከሦ​ስቱ ይልቅ የከ​በረ ነበር፤ አለ​ቃ​ቸ​ውም ሆነ፤ ነገር ግን ወደ ሦስቱ አል​ደ​ረ​ሰም።


አን​ዱም ሌላ​ውን ቢያ​ሸ​ንፍ ሁለቱ በፊቱ ይቆ​ማሉ፤ በሦ​ስ​ትም የተ​ገ​መደ ገመድ ፈጥኖ አይ​በ​ጠ​ስም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios