La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 21:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በገ​ባ​ዖ​ንም ሰዎች እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት በተ​ራ​ራው ላይ ሰቀ​ሏ​ቸው። ሰባ​ቱም በአ​ን​ድ​ነት ወደቁ፤ እህል በሚ​ታ​ጨ​ድ​በ​ትም ወራት በገ​ብሱ መከር መጀ​መ​ሪያ ተገ​ደሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለገባዖናውያን አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ገድለው በኰረብታው ላይ በእግዚአብሔር ፊት ሰቀሏቸው። ሰባቱም በአንድነት ወደቁ፤ የተገደሉትም በመከሩ ወራት የመጀመሪያ ቀኖች፣ የገብስ ዐጨዳ በተጀመረበት ዕለት ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም ለገባዖናውያን አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ገድለው በኰረብታው ላይ በጌታ ፊት ሰቀሏቸው። ሰባቱም በአንድነት ሞቱ፤ የተገደሉትም እህል በሚታጨድበት ወራት በገብሱ መከር መጀመሪያ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዳዊት እነዚህን ሁሉ ለገባዖን ሰዎች አሳልፎ ሰጠ፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት በተራራው ላይ ሰቀሉአቸው፤ ሰባቱም በአንድነት ሞቱ፤ እነርሱም የተገደሉት በጸደይ ወራት ማለቂያና በገብስ መከር መጀመሪያ ላይ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለገባዖንም ሰዎች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ በእግዚአብሔርም ፊት በተራራው ላይ ሰቀሉአቸው፥ ሰባቱም በአንድነት ወደቁ፥ እህል በሚታጨድበት ወራት በገብሱ መከር መጀመሪያ ተገደሉ።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 21:9
13 Referencias Cruzadas  

ከል​ጆቹ ሰባት ሰዎች ስጠ​ንና ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​መ​ረ​ጠው በሳ​ኦል ሀገር በገ​ባ​ዖን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ሠ​ቅ​ላ​ቸ​ዋ​ለን።” ንጉ​ሡም፥ “እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ” አለ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት አም​ጥ​ተው ዳዊት በተ​ከ​ለ​ላት ድን​ኳን ውስጥ በስ​ፍ​ራዋ አኖ​ሩ​አት፤ ዳዊ​ትም የሚ​ቃ​ጠ​ልና የሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕ​ትን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አሳ​ረገ።


ዳዊ​ትም ሜል​ኮ​ልን፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዘም​ሬ​አ​ለሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ከአ​ባ​ት​ሽና ከቤቱ ሁሉ ይልቅ የመ​ረ​ጠኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ሰ​ገነ ይሁን፤ ስለ​ዚ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጫ​ወ​ታ​ለሁ፤ እዘ​ም​ራ​ለ​ሁም፤


አት​ስ​ገ​ድ​ላ​ቸው፤ አታ​ም​ል​ካ​ቸ​ውም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ቀና​ተኛ አም​ላክ ነኝና። በሚ​ጠ​ሉኝ እስከ ሦስ​ተ​ኛና አራ​ተኛ ትው​ልድ ድረስ የአ​ባ​ቶ​ችን ኀጢ​አት በል​ጆች ላይ የማ​መጣ፤


ተል​ባ​ውና ገብሱ ተመታ፤ ገብሱ አሽቶ፥ ተል​ባ​ውም አፍ​ርቶ ነበ​ርና።


ስን​ዴ​ውና አጃው ግን አል​ተ​መ​ቱም፤ ገና ቡቃያ ነበ​ሩና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ስላ​ፈ​ረሱ የሕ​ዝ​ቡን አለ​ቆች ሁሉ ወስ​ደህ በፀ​ሐይ ፊት ቅጣ​ቸው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ ከእ​ስ​ራ​ኤል ይር​ቃል።”


“ማንም ሰው ለሞት የሚ​ያ​በ​ቃ​ውን ኀጢ​አት ቢሠራ፥ እን​ዲ​ሞ​ትም ቢፈ​ረ​ድ​በት፥ በእ​ን​ጨ​ትም ላይ ብት​ሰ​ቅ​ለው፥


ኑኃሚንም ከእርስዋም ጋር ከሞዓብ ምድር የተመለሰችው ሞዓባዊቱ ምራትዋ ሩት ተመለሱ። የገብስም መከር በተጀመረ ጊዜ ወደ ቤተልሔም መጡ።


ሳሙ​ኤ​ልም አጋ​ግን፥ “ሰይ​ፍህ ሴቶ​ችን ልጆች አልባ እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ቻ​ቸው እን​ዲሁ እና​ትህ በሴ​ቶች መካ​ከል ልጅ አልባ ትሆ​ና​ለች” አለ፥ ሳሙ​ኤ​ልም አጋ​ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በጌ​ል​ጌላ ወጋው።