በዐሥራ አራተኛውም ዓመት ኮሎዶጎሞርና ከእርሱ ጋር የነበሩት ነገሥታት መጡ፤ ረዐይትን በአስጣሮት ቃርናይም፥ ከእነርሱም ጋር ጽኑዓን ሰዎችንና ኦሚዎስን በሴዊ ከተማ ገደሉአቸው፤
2 ሳሙኤል 21:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከራፋይም ወገን የነበረው ኤስቢ መጣ፤ የጦሩም ሚዛን ክብደት ሦስት መቶ ሰቅል ናስ ነበር። አዲስ የጦር መሣሪያም ታጥቆ ነበር፤ ዳዊትንም ሊገድለው ፈለገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነ ይሽቢብኖብ የተባለ፣ የናስ ጦሩ ሦስት መቶ ሰቅል የሚመዝንና አዲስ ሰይፍ የታጠቀ ሰው ነበረ፤ እርሱም ዳዊትን ለመግደል ዐሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነ ይሽቢበኖብ የተባለ ዳዊትን ለመግደል አሰበ። የናስ ጦሩ ሦስት መቶ ሰቅል የሚመዝንና አዲስ ሰይፍ የታጠቀ ሰው ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሦስት ኪሎ ተኩል የሚመዝን ከነሐስ የተሠራ ጦር የያዘና አዲስ ሰይፍ የታጠቀ ዩሽቢበኖብ ተብሎ የሚጠራ አንድ ኀያል ሰው ዳዊትን ለመግደል አስቦ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከራፋይም ወገን የነበረው ይሽቢብኖብ ዳዊትን ይገድል ዘንድ አሰበ፥ የጦሩም ሚዛን ክብደት ሦስት መቶ ሰቅል ናስ ነበረ፥ አዲስም የጦር መሣሪያ ታጥቆ ነበር። |
በዐሥራ አራተኛውም ዓመት ኮሎዶጎሞርና ከእርሱ ጋር የነበሩት ነገሥታት መጡ፤ ረዐይትን በአስጣሮት ቃርናይም፥ ከእነርሱም ጋር ጽኑዓን ሰዎችንና ኦሚዎስን በሴዊ ከተማ ገደሉአቸው፤
በእነዚያም ወራት ረዓይት በምድር ላይ ነበሩ። ከዚያም በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች ወደ ሰው ሴቶች ልጆች በገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው፤ እነርሱም በዱሮ ዘመን ስማቸውን ያስጠሩ ኀያላን ሰዎች ሆኑ።
ከዚህም በኋላ እንደ ገና በጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት ሆነ፤ ያን ጊዜም አስጣጦታዊው ሴቤኮይ ከራፋይም ወገን የሆነውን ሳፍን ገደለው።
ደግሞም በጌት ላይ ጦርነት ሆነ፤ በዚያም በእጁና በእግሩ ስድስት ስድስትሁላሁሉ ሃያ አራት ጣቶች የነበሩት አንድ ረዥም ሰው ነበረ፤ እርሱ ደግሞ ከራፋይም የተወለደ ነበረ።
እነዚያም አራቱ በጌት ውስጥ ከረዐይት የተወለዱ የራፋይም ወገኖች ነበሩ፤ በዳዊትም እጅ በአገልጋዮቹም እጅ ወደቁ።
ወደ ምድረ በዳም ወጡ፤ ወደ ኬብሮንም ደረሱ፤ በዚያም የዔናቅ ዘሮች አኪማን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ኬብሮንም በግብፅ ካለችው ከጣኔዎስ ከተማ በፊት ሰባት ዓመታት ተሠርታ ነበር።
ወዴት እንወጣለን? ሕዝቡ ታላቅና ብዙ ነው፤ ከእኛም ይጠነክራሉ፤ ከተሞቹም ታላላቆች፥ የተመሸጉም፥ እስከ ሰማይም የደረሱ ናቸው፤ የረዐይትንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየናቸው ብለው ወንድሞቻችን ልባችንን አስፈሩት።’
እነርሱም እንደ ዔናቃውያን ታላቅና ብዙ፥ ጽኑዓንም ሕዝብ ነበሩ፤ እግዚአብሔርም ከፊታቸው አጠፋቸው፤ እነርሱንም አሳድደው በስፍራቸው ተቀመጡ።
ከራፋይንም ወገን የባሳን ንጉሥ ዐግ ብቻውን ቀርቶ ነበር፤ እነሆ፥ አልጋው የብረት አልጋ ነበረ፤ እርሱ በአሞን ልጆች ሀገር ዳርቻ አለ፤ ርዝመቱ ዘጠኝ ክንድ ወርዱም አራት ክንድ በሰው ክንድ ልክ ነበረ።
አንተም የምታውቃቸው፥ ስለ እነርሱም፦ በዔናቅ ልጆች ፊት መቆም ማን ይችላል? ሲባል የሰማኸው ታላቅ፥ ብዙና ረዥም ሕዝብ የዔናቅ ልጆች ናቸው።