የእርሱም በምትሆን በሁለተኛይቱ ሰረገላ አስቀመጠው፤ ስገዱ እያለም በፊት በፊቱ አዋጅ ነጋሪ እንዲሄድ አደረገ፤ በግብፅ ምድር ሁሉ ላይም ሾመው።
2 ሳሙኤል 20:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢያዕር ሰው ኢራስም ለዳዊት ካህን ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም የኢያዕር ሰው ዒራስ የዳዊት አማካሪ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም የያኢር ሰው ዒራ የዳዊት ካህን ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም የያዒር ከተማ ተወላጅ የሆነው ዒራ ከዳዊት ካህናት አንዱ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኢያዕር ሰውም ዒራስ ለዳዊት አማካሪ ነበረ። |
የእርሱም በምትሆን በሁለተኛይቱ ሰረገላ አስቀመጠው፤ ስገዱ እያለም በፊት በፊቱ አዋጅ ነጋሪ እንዲሄድ አደረገ፤ በግብፅ ምድር ሁሉ ላይም ሾመው።
ፈርዖንም የዮሴፍን ስም “እስፍንቶፎኔህ” ብሎ ጠራው፤ የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጴጤፌራ ልጅ የምትሆን አስኔትንም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው።
በዳዊትም ዘመን ሦስት ዓመት ያህል በተከታታይ ራብ ሆነ፤ ዳዊትም የእግዚአብሔርን ቃል ጠየቀ። እግዚአብሔርም አለ፥ “የገባዖንን ሰዎች ስለ ገደለ በሳኦልና በቤቱ ላይ ደም አለበት፥”
የአሳፍም ልጆች መዘምራን እንደ ዳዊት፥ እንደ አሳፍም፥ እንደ ኤማንም የንጉሡም ባለ ራእይ እንደ ነበረው እንደ ኤዶትም ትእዛዝ በየስፍራቸው ነበሩ፤ በረኞቹም በሮቹን ሁሉ ይጠብቁ ነበር፤ ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ያዘጋጁላቸው ነበርና ከአገልግሎታቸው ይርቁ ዘንድ አያስፈልጋቸውም ነበር።
ወንድሙን የሚበድለው ያም ሰው፥ “በእኛ ላይ አንተን አለቃ ወይስ ዳኛ ማን አደረገህ? ወይስ ግብፃዊውን ትናንት እንደ ገደልኸው ልትገድለኝ ትሻለህን?” አለው። ሙሴም፥ “በእውነት ይህ ነገር ታውቆአልን?” ብሎ ፈራ።
ለምድያምም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ የአባታቸውንም የዮቶርን በጎች ይጠብቁ ነበር፤ እነርሱም መጥተው ውኃ ቀዱ፤ የአባታቸውንም የዮቶርን በጎች ሊያጠጡ የውኃዉን ገንዳ ሞሉ።
የምናሴ ልጅ ኢያዕር እስከ ጌርጋሴና እስከ መካቲ ዳርቻ ድረስ የአርጎብን አውራጃ ሁሉ ወሰደ፤ ይህችንም የባሳንን ምድር እስከዚች ቀን ድረስ በስሙ አውታይ ኢያዕር ብሎ ጠራ።