ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ተሰብስበው መጡ። ኀዘኑንም ያስተዉት ዘንድ አባታቸውን ማለዱት። ኀዘኑንም መተውን እንቢ አለ፥ እንዲህም አላቸው፥ “ወደ ልጄ ወደ መቃብር እያዘንሁ እወርዳለሁ።” አባቱም ስለ እርሱ አለቀሰ።
2 ሳሙኤል 19:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለኢዮአብ፥ “ንጉሡ ስለ አቤሴሎም ያዝናል፤ ያለቅሳልም” ብለው ነገሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለኢዮአብ፣ “ንጉሡ ዳዊት ስለ ልጁ ስለ አቤሴሎም እያለቀሰ እያዘነ ነው” ተብሎ ተነገረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም እጅግ አዘነ፤ በቅጽር በሩ ዐናት ላይ ወዳለችው ቤት ወጥቶ አለቀሰ፤ ሲሄድም፥ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ! ልጄ አቤሴሎም! በአንተ ፈንታ ምነው እኔ በሞትሁ ኖሮ! አቤሴሎም፥ ልጄን፥ ወየው ልጄን!” ይል ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ዳዊት ስለ ልጁ ስለ አቤሴሎም ሞት በብርቱ አዝኖ በማልቀስ ላይ መሆኑን ኢዮአብ ሰማ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብም ንጉሡ ስለ አቤሴሎም እንዳለቀሰና ዋይ ዋይ እንዳለ ሰማ። |
ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ተሰብስበው መጡ። ኀዘኑንም ያስተዉት ዘንድ አባታቸውን ማለዱት። ኀዘኑንም መተውን እንቢ አለ፥ እንዲህም አላቸው፥ “ወደ ልጄ ወደ መቃብር እያዘንሁ እወርዳለሁ።” አባቱም ስለ እርሱ አለቀሰ።
ሰውየውም ኢዮአብን፥ “ንጉሡ አንተንና አቢሳን፥ ኤቲንም፦ ብላቴናውን አቤሴሎምን ጠብቁ ብሎ ሲያዝ እኛ በጆሮአችን ሰምተናልና ሺህ ሰቅል ብር በእጄ ላይ ብትመዝን እጄን በንጉሡ ልጅ ላይ አልዘረጋም ነበር።
ኢዮአብም፥ “እኔ ከአንተ ጋር እንዲህ እዘገይ ዘንድ አልችልም” ብሎ ሦስት ጦሮች በእጁ ወሰደ፤ አቤሴሎምም ገና በዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ ሕያው ሳለ በልቡ ላይ ተከላቸው።
ኢዮአብም፥ “አንተ በዚች ቀን የምሥራች የምትናገር ሰው አይደለህም፤ ወሬውን በሌላ ቀን ትናገራለህ፤ በዚች ቀን ግን የንጉሡ ልጅ እንደ ሞተ ወሬ አትናገርም” አለው።
ንጉሡም እጅግ ደነገጠ፤ በበሩም ላይ ወዳለችው ሰገነት ወጥቶ አለቀሰ፤ ሲሄድም፥ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ፥ ልጄ፥ ልጄ አቤሴሎም ሆይ፥ በአንተ ፋንታ እኔ እንድሞት ቤዛህም እንድሆን ማን ባደረገኝ፥ ልጄ አቤሴሎም፥ ልጄ ሆይ፥” ይል ነበር።
ንጉሡም ኢዮአብንና አቢሳን ኤቲንም፥ “ለብላቴናው ለአቤሴሎም ስለ እኔ ራሩለት” ብሎ አዘዛቸው። ንጉሡም ስለ አቤሴሎም አለቆቹን ሁሉ ሲያዝዝ ሕዝቡ ሁሉ ሰሙ።
በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፣ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።