Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ሳሙኤል 18:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ሰው​የ​ውም ኢዮ​አ​ብን፥ “ንጉሡ አን​ተ​ንና አቢ​ሳን፥ ኤቲ​ንም፦ ብላ​ቴ​ና​ውን አቤ​ሴ​ሎ​ምን ጠብቁ ብሎ ሲያዝ እኛ በጆ​ሮ​አ​ችን ሰም​ተ​ና​ልና ሺህ ሰቅል ብር በእጄ ላይ ብት​መ​ዝን እጄን በን​ጉሡ ልጅ ላይ አል​ዘ​ረ​ጋም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሰውየው ግን ለኢዮአብ እንዲህ አለው፤ “እኛ እየሰማን ንጉሡ፣ ‘ወጣቱ አቤሴሎም ጕዳት እንዳያገኘው ስለ እኔ ብላችሁ ጠብቁት’ ብሎ አንተን፣ አቢሳንና ኢታይን ያዘዛችሁ ስለ ሆነ፣ አንድ ሺሕ ሰቅል ጥሬ ብር በእጄ ላይ ቢመዘንልኝ እንኳ፣ በንጉሡ ልጅ ላይ እጄን አላነሣም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ሰውየው ግን ለኢዮአብ እንዲህ አለ፤ “እኛ እየሰማን ንጉሡ፥ ‘ወጣቱ አቤሴሎም ጉዳት እንዳያገኘው ስለ እኔ ብላችሁ ጠብቁት’ ተብሎ አንተን፥ አቢሳንና ኢታይን ያዘዛችሁ ስለሆነ፥ አንድ ሺህ ብር በእጄ ላይ ቢመዘንልኝ እንኳ፥ በንጉሡ ልጅ ላይ እጄን አላነሣም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ሰውየው ግን እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አንድ ሺህ ጥሬ ብር እንኳ ብትሰጠኝ በንጉሡ ልጅ ላይ እጄን አላነሣም፤ ንጉሡ ለአንተ፥ ለአቢሳና ለኢታይ ‘ለእኔ ስትሉ በወጣቱ አቤሴሎም ላይ ለሞት የሚያደርስ ጒዳት እንዳታደርሱበት’ ሲል የሰጣችሁን ትእዛዝ ሁላችንም ሰምተናል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ሰውዮውም ኢዮአብን፦ እኛ ስንሰማ ንጉሡ አንተንና አቢሳን ኢታይንም፦ ብላቴናውን አቤሴሎምን ማንም እንዳይነካው ተጠንቀቁ ብሎ አዝዞአልና ሺህ ብር በእጄ ላይ ብትመዝን እጄን በንጉሡ ልጅ ላይ ባልዘረጋሁም ነበር አለው።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 18:12
3 Referencias Cruzadas  

ኢዮ​አ​ብም ለነ​ገ​ረው ሰው፥ “እነሆ፥ ካየ​ኸው ለምን በም​ድር ላይ አል​ገ​ደ​ል​ኸ​ውም? ዐሥር ብርና አንድ ድግ እሰ​ጥህ ነበር” አለው።


ንጉ​ሡም ኢዮ​አ​ብ​ንና አቢ​ሳን ኤቲ​ንም፥ “ለብ​ላ​ቴ​ናው ለአ​ቤ​ሴ​ሎም ስለ እኔ ራሩ​ለት” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው። ንጉ​ሡም ስለ አቤ​ሴ​ሎም አለ​ቆ​ቹን ሁሉ ሲያ​ዝዝ ሕዝቡ ሁሉ ሰሙ።


ለኢ​ዮ​አብ፥ “ንጉሡ ስለ አቤ​ሴ​ሎም ያዝ​ናል፤ ያለ​ቅ​ሳ​ልም” ብለው ነገ​ሩት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos