2 ሳሙኤል 18:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ንጉሡም ኢዮአብንና አቢሳን ኤቲንም፥ “ለብላቴናው ለአቤሴሎም ስለ እኔ ራሩለት” ብሎ አዘዛቸው። ንጉሡም ስለ አቤሴሎም አለቆቹን ሁሉ ሲያዝዝ ሕዝቡ ሁሉ ሰሙ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ንጉሡም ኢዮአብን፣ አቢሳንና ኢታይን፣ “ለእኔ ስትሉ በወጣቱ ልጄ በአቤሴሎም ላይ ጕዳት እንዳታደርሱበት” ብሎ አዘዛቸው። ንጉሡ ልጁን አቤሴሎምን አስመልክቶ ለእያንዳንዱ አዛዥ ትእዛዝ ሲሰጥ ሰራዊቱ ሁሉ ሰማ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ንጉሡም ኢዮአብን፥ አቢሳንና ኢታይን፥ “ለእኔ ስትሉ በወጣቱ ልጄ በኤቤሴሎም ላይ ጉዳት እንዳታደርሱበት” ብሎ አዘዛቸው። ንጉሡ ልጁን አቤሴሎምን አስመልክቶ ለአዛዥዎቹ ትእዛዝ ሲሰጥ ሕዝቡ ሁሉ ሰማ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ለኢዮአብ፥ ለአቢሳና ለኢታይም “ለእኔ ስትሉ በወጣቱ በአቤሴሎም ላይ ለሞት የሚያደርስ ጒዳት እንዳታደርሱበት” የሚል ትእዛዝ ሰጣቸው፤ ዳዊት ይህን ትእዛዝ ለጦር አዛዦቹ በሰጠ ጊዜም ወታደሮቹ ሁሉ ይሰሙ ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ንጉሡም ኢዮአብንና አቢሳን ኢታይንም፦ ለብላቴናው ለአቤሴሎም ስለ እኔ ራሩለት ብሎ አዘዛቸው። ንጉሡም ስለ አቤሴሎም አለቆቹን ሁሉ ሲያዝዝ ሕዝቡ ሁሉ ሰማ። Ver Capítulo |