እኔ እንዲህ እመክርሃለሁ፤ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉ እስራኤል ሁሉ ብዛታቸው እንደ ባሕር አሸዋ ሆኖ ወደ አንተ ይሰብሰቡ፤ አንተም በመካከላቸው ትሄዳለህ።
2 ሳሙኤል 18:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ሕዝቡን ከኢዮአብ እጅ በታች ሢሶውን፥ ከኢዮአብም ወንድም ከሶርህያ ልጅ ከአቢሳ እጅ በታች ሢሶውን፥ ከጌት ሰውም ከኤቲ እጅ በታች ሢሶውን ላከ። ዳዊትም ሕዝቡን፥ “እኔ ደግሞ ከእናንተ ጋር እወጣለሁ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም ሰራዊቱን ሲሦውን በኢዮአብ፣ ሲሦውን በኢዮአብ ወንድም በጽሩያ ልጅ በአቢሳ፣ ሲሦውን ደግሞ በጋታዊው በኢታይ አዛዥነት ሥር ላካቸው። ንጉሡም ለሰራዊቱ፣ “እኔ ራሴም ዐብሬአችሁ በርግጥ እወጣለሁ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሠራዊቱን ሲሦውን በኢዮአብ፥ ሲሦውን በኢዮአብ ወንድም በጽሩያ ልጅ በአቢሳይ፥ ሲሦውን ደግሞ በጌታዊው በኢታይ አዛዥነት ሥር ላካቸው። ንጉሡም ለሠራዊቱ፥ “እኔ ራሴም አብሬአችሁ እወጣለሁ” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ሦስት ክፍል አድርጎ ላካቸው፤ ኢዮአብን የሢሶው፥ አቢሳይ የሢሶው፥ እንዲሁም የጋት ተወላጅ የሆነው ኢታይ የሢሶው አዛዦች ሆኑ፤ ንጉሡም ተከታዮቹን “እኔም ራሴ አብሬአችሁ እሄዳለሁ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ሕዝቡን ከኢዮአብ እጅ በታች ሢሶውን፥ ከኢዮአብም ወንድም ከጽሩያ ልጅ ከአቢሳ እጅ በታች ሢሶውን፥ ከጌት ሰውም ከኢታይ እጅ በታች ሢሶውን ሰደደ። ንጉሡም ሕዝቡን፦ እኔ ደግሞ ከእናንተ ጋር እወጣለሁ አላቸው። |
እኔ እንዲህ እመክርሃለሁ፤ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉ እስራኤል ሁሉ ብዛታቸው እንደ ባሕር አሸዋ ሆኖ ወደ አንተ ይሰብሰቡ፤ አንተም በመካከላቸው ትሄዳለህ።
የሶርህያም ልጅ አቢሳ አዳነው፤ ፍልስጥኤማዊውንም ወግቶ ገደለው። ያንጊዜም የዳዊት ሰዎች፥ “አንተ የእስራኤል መብራት እንዳትጠፋ ከእንግዲህ ወዲህ ከእኛ ጋር ለሰልፍ አትወጣም” ብለው ማሉለት።
የሶርህያም ልጅ የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበር። እርሱም ጦሩን በሦስቱ መቶ ላይ አንሥቶ ገደላቸው፤ ስሙም በሦስቱ ዘንድ ተጠርቶ ነበር።
ለሶርህያ ልጅ ለኢዮአብም ወሬ ደረሰለት፤ ኢዮአብ ከአዶንያስ ጋር ተባብሮ ተከተለው እንጂ ከሰሎሞን ጋር አልተባበረም፤ አልተከተለውምም ነበርና። ኢዮአብም ወደ እግዚአብሔር ድንኳን ሸሽቶ የመሠዊያውን ቀንድ ያዘ።
ጌዴዎንም፥ ከእርሱም ጋር የነበሩት መቶ ሰዎች በመካከለኛው ትጋት መጀመሪያ ዘብ ጠባቂዎች ሳይነቁ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ መጡ፤ ቀንደ መለከቶችንም ነፉ፤ በእጃቸውም የነበሩትን ማሰሮዎች ሰባበሩ፤
ሕዝቡንም ወስዶ በሦስት ወገን ከፈላቸው፤ በሜዳም ሸመቀ፤ ተመለከተም፤ እነሆም፥ ሕዝቡ ከከተማ ወጡ፤ ተነሣባቸውም፤ ገደላቸውም።
በነጋውም ሳኦል ሕዝቡን በሦስት ወገን አደረጋቸው፤ወገግም ባለ ጊዜ ወደ ሰፈሩ መካከል ገቡ፤ ቀትርም እስኪሆን ድረስ አሞናውያንን መቱ፤ የቀሩትም ተበተኑ፤ ከውስጣቸውም ሁለት በአንድ ላይ ሆነው አልተገኙም።