Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 7:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ሦስ​ቱ​ንም መቶ ሰዎች በሦ​ስት ወገን ከፈ​ላ​ቸው፤ በሁ​ሉም እጅ ቀንደ መለ​ከ​ትና ባዶ ማሰሮ፥ በማ​ሰ​ሮ​ዉም ውስጥ ችቦ ሰጣ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ሦስቱን መቶ ሰዎች በሦስት ቡድን ከፍሎ፣ እያንዳንዱን ሰው ቀንደ መለከትና በውስጡ ችቦ ያለበት ባዶ ማሰሮ በእጁ እንዲይዝ አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ሦስቱን መቶ ሰዎች በሦስት ቡድን ከፍሎ፥ እያንዳንዱን ሰው ቀንደ መለከትና በውስጡ ችቦ ያለበት ባዶ ማሰሮ በእጁ እንዲይዝ አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ሦስት መቶዎቹንም ሰዎች ከፍሎ በሦስት ቡድን መደባቸው፤ ለእያንዳንዱም ሰው አንድ እምቢልታና በውስጡ ችቦ ያለበት አንድ ማሰሮ ሰጠ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ሦስቱንም መቶ ሰዎች በሦስት ወገን ከፈላቸው፥ በሁሉም እጅ ቀንደ መለከትና ባዶ ማሰሮ፥ በማሰሮውም ውስጥ ችቦ ሰጠ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 7:16
6 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ከእኛ ያይ​ደለ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ገኘ ታላቅ ኀይል ይሆን ዘንድ በሸ​ክላ ዕቃ ውስጥ ይህ መዝ​ገብ አለን።


እር​ሱም ከብ​ላ​ቴ​ኖቹ ጋር በሌ​ሊት ደረ​ሰ​ባ​ቸው፤ መታ​ቸ​ውም፤ በደ​ማ​ስቆ ግራ እስ​ካ​ለ​ች​ውም እስከ ሖባ ድረስ አሳ​ደ​ዳ​ቸው።


ጌዴ​ዎ​ንም ሕል​ሙ​ንና ትር​ጓ​ሜ​ዉን በሰማ ጊዜ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገደ፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ሰፈር ተመ​ልሶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ያ​ምን ሠራ​ዊት በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ልና ተነሡ” አለ።


እር​ሱም፥ “እኔን ተመ​ል​ከቱ፤ እን​ዲ​ሁም አድ​ርጉ፤ እነ​ሆም፥ ወደ ሰፈሩ ዳርቻ በደ​ረ​ስሁ ጊዜ እኔ እን​ደ​ማ​ደ​ርግ እን​ዲሁ እና​ንተ አድ​ርጉ፤


በነ​ጋ​ውም ሳኦል ሕዝ​ቡን በሦ​ስት ወገን አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ወገ​ግም ባለ ጊዜ ወደ ሰፈሩ መካ​ከል ገቡ፤ ቀት​ርም እስ​ኪ​ሆን ድረስ አሞ​ና​ው​ያ​ንን መቱ፤ የቀ​ሩ​ትም ተበ​ተኑ፤ ከው​ስ​ጣ​ቸ​ውም ሁለት በአ​ንድ ላይ ሆነው አል​ተ​ገ​ኙም።


ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡን ከኢ​ዮ​አብ እጅ በታች ሢሶ​ውን፥ ከኢ​ዮ​አ​ብም ወን​ድም ከሶ​ር​ህያ ልጅ ከአ​ቢሳ እጅ በታች ሢሶ​ውን፥ ከጌት ሰውም ከኤቲ እጅ በታች ሢሶ​ውን ላከ። ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡን፥ “እኔ ደግሞ ከእ​ና​ንተ ጋር እወ​ጣ​ለሁ” አላ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios