2 ሳሙኤል 17:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ እንዲህ እመክርሃለሁ፤ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉ እስራኤል ሁሉ ብዛታቸው እንደ ባሕር አሸዋ ሆኖ ወደ አንተ ይሰብሰቡ፤ አንተም በመካከላቸው ትሄዳለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንግዲህ እኔ የምመክርህ ይህ ነው፤ ቍጥሩ እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የበዛው፣ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያለው እስራኤል ሁሉ ወደ አንተ ይሰብሰብና አንተው ራስህ ወደ ጦርነቱ ምራው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ የምመክርህ፥ ቁጥሩ እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የበዛው፥ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያለው እስራኤል ሁሉ ወዳንተ ይሰብሰብና አንተው ራስህ ወደ ጦርነቱ ምራው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እኔ የምመክርህ፥ ከአገሪቱ አራት ማእዘኖች ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉትንና ብዛታቸው እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የሆነው እስራኤላውያን ሁሉ በአንድነት ሰብስበህ አንተው ራስህ አዛዥ በመሆን ወደ ጦርነቱ እንድትመራቸው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን የምመክርህ ይህ ነው፥ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያለ እስራኤል ሁሉ በብዛቱ እንደ ባሕር አሸዋ ሆኖ ወደ አንተ ይሰብሰብ፥ አንተም በመካከላቸው ወደ ሰልፍ ውጣ። |
አብርሃምም ማልዶ ተነሣ፤ እንጀራንም ወሰደ፤ የውኃ አቍማዳንም ለአጋር በትከሻዋ አሸከማት፤ ሕፃኑንም ሰጥቶ አስወጣት፤ እርስዋም ሄደች፤ በዐዘቅተ መሐላም በኩል ባለው ምድረ በዳ ተቅበዘበዘች።
ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ፈጽሞ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላት ሀገሮችን ይወርሳሉ፤
አሁንም ከተማዪቱን እኔ ቀድሜ እንዳልይዝ፥ በስሜም እንዳትጠራ፥ የቀረውን ሕዝብ ሰብስብ፥ ከተማዪቱንም ከብበህ ቀድመህ ያዛት።”
ንጉሡም ከእርሱ ጋር የነበረውን የሠራዊት አለቃ ኢዮአብን፥ “የሕዝቡን ድምር አውቅ ዘንድ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ሂድ፤ ሕዝቡንም ቍጠራቸው” አለው።
የዳዊትንም ዙፋን በእስራኤልና በይሁዳ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ከፍ ያደርግ ዘንድ መንግሥትን ከሳኦል ቤት ወሰዳት።”
ሁለት የሐሰት ምስክሮችንም በፊቱ አስቀምጡና፦ እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል ብለው ይመስክሩበት፤ አውጥታችሁም እስኪሞት ድረስ በድንጋይ መትታችሁ ግደሉት።”
እነርሱ፥ ከእነርሱም ጋር ሠራዊቶቻቸው ሁሉ ብዛታቸው እንደ ባሕር አሸዋ ሆነው ወጡ፤ ፈረሶችና ሰረገሎችም እጅግ ብዙዎች ነበሩ።
የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ወጡ፤ ማኅበሩም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ፥ ከገለዓድም ሰዎች ጋር፥ ወደ እግዚአብሔር ወደ መሴፋ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ።
ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት ተሰበሰቡ፤ ሠላሳ ሺህ ሰረገሎች፥ ስድስት ሺህም ፈረሰኞች፥ በባሕርም ዳር እንዳለ አሸዋ ብዙ ሕዝብ ነበሩ፤ ወጥተውም ከቤቶሮን በአዜብ በኩል በማኪማስ ሰፈሩ።