1 ሳሙኤል 13:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት ተሰበሰቡ፤ ሠላሳ ሺህ ሰረገሎች፥ ስድስት ሺህም ፈረሰኞች፥ በባሕርም ዳር እንዳለ አሸዋ ብዙ ሕዝብ ነበሩ፤ ወጥተውም ከቤቶሮን በአዜብ በኩል በማኪማስ ሰፈሩ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ፍልስጥኤማውያን ሦስት ሺሕ ሠረገሎች፣ ስድስት ሺሕ ፈረሰኞች ቍጥሩ እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ ሰራዊት ይዘው እስራኤልን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ ወጥተውም ከቤትአዌን በስተምሥራቅ ባለችው በማክማስ ሰፈሩ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ፍልስጥኤማውያን ሠላሳ ሺህ ሠረገሎች፥ ስድስት ሺህ ፈረሰኞች ቁጥሩ እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ ሠራዊት ይዘው እስራኤልን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ ወጥተውም ከቤትአዌን በስተ ምሥራቅ ባለችው በማክማስ ሰፈሩ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ፍልስጥኤማውያንም እስራኤላውያንን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ እነርሱም ከሠላሳ ሺህ የጦር ሠረገሎችና ከስድስት ሺህ ፈረሰኞች ጋር ብዛቱ እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የበዛ ሠራዊት ነበራቸው፤ ሄደውም በቤትአዌን በስተምሥራቅ ሚክማስ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ መሸጉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት ተሰበሰቡ፥ ሠላሳ ሺህ ሰረገሎች ስድስትም ሺህ ፈረሰኞች በባሕርም ዳር እንዳለ አሸዋ ብዙ ሕዝብ ነበሩ፥ ወጥተውም ከቤትአዌን በምሥራቅ በኩል በማክማስ ሰፈሩ። Ver Capítulo |