2 ጴጥሮስ 1:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ ባሕርያት ተትረፍርፈው ቢኖሯችሁ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ ዳተኞችና ፍሬ ቢሶች ከመሆን ይጠብቋችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ ነገሮች ቢኖሩአችሁና ቢበዙላችሁ፥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ በተመለከተ ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጓችኋልና፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ ነገሮች በብዛት ቢኖሩአችሁ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለማወቅ የማትጠቅሙ ፍሬቢሶች እንዳትሆኑ ይጠብቁአችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና፤ |
በእኔ ያለውን፥ ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍም ሁሉ ያስወግደዋል፤ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ግን በብዙ እንዲያፈራ ያጠራዋል።
ብቻህን እውነተኛ አምላክ የሆንህ አንተን፥ የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘለዓለም ሕይወት ናት።
አሁንም የተወደዳችሁ ወንድሞቻችን ሆይ፥ የጸናችሁና የማትናወጡ ሁኑ፤ ዘወትር በጎ ምግባርን አብዝታችሁ ለእግዚአብሔር አበርክቱ፤ ስለ ጌታችን መድከማችሁ ለከንቱ እንዳይደለ ታውቃላችሁና።
በሃይማኖት ጸንታችሁ እንደ ሆነ ራሳችሁን መርምሩ፤ እናንተ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናንተ ጋር እንዳለ አታውቁምን? እንዲህ ካልሆነ ግን እናንተ የተናቃችሁ ናችሁ።
በብዙ መከራ ከመፈተናቸው የተነሣ ደስታቸው በዝቶአልና፤ በድህነታቸው ጥልቅነትም የለጋስነታቸው ባለጠግነት በዝታለችና።
በሁሉ ነገር በእምነትና በቃል፥ በዕውቀትም፥ በትጋትም በእናንተ ዘንድ በሆነው ሁሉ እኛን በመውደዳችሁ ፍጹማን እንደ ሆናችሁ፥ እንዲሁም ደግሞ ይህቺን ስጦታ አብዙ።
ክርስቶስን አገለግለው ዘንድ፥ ሁሉን የተውሁለት፥ እንደ ጕድፍም ያደረግሁለት የጌታዬን የኢየሱስ ክርስቶስን ኀይልና ገናናነት ስለማውቅ ሁሉን እንደ ኢምንት ቈጠርሁት።
ወደ እግዚአብሔር በሚገባችሁ ትሄዱ ዘንድ፥ በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ፥ እግዚአብሔርንም በማወቅ እያደጋችሁ፥ በሁሉ ደስ ታሰኙት ዘንድ።
በጥበብ ሁሉ እንድትበለጽጉ የእግዚአብሔር ቃል በእናንተ ዘንድ ይጽና፤ በመንፈስም ራሳችሁን አስተምሩ፤ ገሥፁ፤ መዝሙርንና ምስጋናን፥ የቅድስና ማሕሌትንም በልባችሁ በጸጋ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።
ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ሲመጣ፥ በአምላካችንና በአባታችን ፊት በቅድስና ነቀፋ የሌለበት አድርጎ ልባችሁን ያጸና ዘንድ፥ እኛ ደግሞ ለእናንተ እንደምንሆን ጌታ እርስ በእርሳችሁ ያላችሁን ለሁሉም የሚሆን ፍቅራችሁን ያብዛ፤ ይጨምርም።
እንግዲህ በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! ልትመላለሱ እግዚአብሔርንም ደስ ልታሰኙ እንዴት እንደሚገባችሁ ከእኛ ዘንድ እንደ ተቀበላችሁ፥ እናንተ ደግሞ እንደምትመላለሱ፥ ከፊት ይልቅ ትበዙ ዘንድ በጌታ በኢየሱስ እንለምናችኋለን፤ እንመክራችሁማለን።
ወንድሞች ሆይ! እምነታችሁ እጅግ ስለሚያድግ፥ የሁላችሁም የእያንዳንዳችሁ ፍቅር እርስ በርሳችሁ ስለሚበዛ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግድ አለብን፤
ከዚህም ጋር ቤት ለቤት እየዞሩ ሥራን መፍታት ደግሞ ይማራሉ፤ የማይገባውንም እየተናገሩ ለፍላፊዎችና በነገር ገቢዎች ይሆናሉ እንጂ፥ ሥራ ፈቶች ብቻ አይደሉም።
የመለኮቱ ኀይል በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።
በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዕውቀት ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ ዳግመኛ በእርስዋ ተጠላልፈው የተሸነፉ ቢሆኑ፥ ከፊተኛው ኑሮአቸው ይልቅ የኋለኛው የባሰ ሆኖባቸዋል።
ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።