Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 5:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍቅር በእ​ና​ንተ እን​ደ​ሌ​ለ​ባ​ችሁ ዐወ​ቅሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 ነገር ግን እናንተን ዐውቃችኋለሁ፤ የእግዚአብሔርም ፍቅር በልባችሁ እንደሌለ ዐውቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 ዳሩ ግን የእግዚአብሔር ፍቅር በውስጣችሁ እንደሌላችሁ ዐወቅሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 እናንተ ከልባችሁ እግዚአብሔርን የማታፈቅሩ መሆናችሁን ዐውቃለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 5:42
17 Referencias Cruzadas  

ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?


ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፥ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል?


ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም።


የሰ​ው​ንም ግብ​ሩን ሊነ​ግ​ሩት አይ​ሻም፤ እርሱ በሰው ያለ​ውን ያውቅ ነበ​ርና።


ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።


የሥጋ ዐሳብ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላቱ ነውና፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ ስለ​ማ​ይ​ገዛ፥ መፈ​ጸም አይ​ቻ​ለ​ውም።


ሦስ​ተኛ ጊዜም፥ “የዮና ልጅ ስም​ዖን ሆይ፥ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ ጴጥ​ሮ​ስም ሦስት ጊዜ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን? ስላ​ለው ተከዘ፤ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታው​ቃ​ለህ፤ እኔም እን​ደ​ም​ወ​ድህ አንተ ታው​ቃ​ለህ” አለው፤ “እን​ኪ​ያስ ግል​ገ​ሎ​ችን ጠብቅ” አለው።


እና​ን​ተም አታ​ው​ቁ​ትም፤ እኔ ግን ኣው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ አላ​ው​ቀ​ውም ብልም እንደ እና​ንተ ሐሰ​ተኛ እሆ​ና​ለሁ፤ እኔ አው​ቀ​ዋ​ለሁ ቃሉ​ንም እጠ​ብ​ቃ​ለሁ።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሆነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ይሰ​ማል፤ ስለ​ዚህ እና​ንተ አት​ሰ​ሙ​ኝም፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምና።”


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አባ​ታ​ችሁ ቢሆ​ንስ እኔን በወ​ደ​ዳ​ች​ሁኝ ነበር፤ እኔ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጥቼ መጥ​ቻ​ለ​ሁና፤ እኔ በገዛ እጄ የመ​ጣሁ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ እርሱ ላከኝ እንጂ።


ከባ​ል​ን​ጀ​ራ​ችሁ ክብ​ርን የም​ት​መ​ርጡ፥ ከአ​ንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብ​ርን የማ​ትሹ እና​ንተ እን​ዴት ልታ​ምኑ ትች​ላ​ላ​ችሁ?


እር​ሱም፥ “እና​ን​ተስ ለሰው ይም​ሰል ትመ​ጻ​ደ​ቃ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልቡ​ና​ች​ሁን ያው​ቃል፤ በሰው ዘንድ የከ​በረ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ናቀ ይሆ​ና​ልና።


እኔ ከሰው ክብ​ርን ልቀ​በል አል​ሻም።


እኔ በአ​ባቴ ስም መጣሁ፥ አል​ተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁ​ኝ​ምም፤ ሌላው ግን በራሱ ስም ቢመጣ እር​ሱን ትቀ​በ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios