ዘበኛውም፥ “የፊተኛው ሩጫ እንደ ሳዶቅ ልጅ እንደ አኪማሖስ ሩጫ ይመስላል” አለ፤ “ንጉሡም፦ እርሱ መልካም ሰው ነው፤ መልካምም ወሬ ያመጣል” አለ።
2 ነገሥት 9:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰላዩም፥ “መልእክተኛው ደረሰባቸው፥ ነገር ግን አልተመለሰም፤ የሚመራው ግን እንደ ናሜሲ ልጅ እንደ ኢዩ ይመራል በችኮላ ይሄዳልና” ብሎ ነገረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠባቂው፣ “መልእክተኛው ከእነርሱ ዘንድ ደርሷል፤ ነገር ግን ይህም ተመልሶ አልመጣም፤ የወታደሮቹ መሪ ሠረገላ አነዳዱ ልክ እንደ ናሜሲ ልጅ እንደ ኢዩ አነዳድ ነው፤ ሲነዳም እንደ እብድ ነው” ሲል አሳወቀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ዘበኛውም እንደገና መልእክተኛው በመምጣት ላይ ወዳለው ጭፍራ ደርሶአል፤ ነገር ግን ተመልሶ አልመጣም” ካለ በኋላ “የጭፍራው መሪ ሠረገላ አነዳዱ እንደ እብድ ሰው ነው! እንዲያውም ልክ ኢዩን ይመስላል!” ሲል ተናገረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ዘበኛውም እንደገና መልእክተኛው በመምጣት ላይ ወዳለው ጭፍራ ደርሶአል፤ ነገር ግን ተመልሶ አልመጣም” ካለ በኋላ “የጭፍራው መሪ ሠረገላ አነዳዱ እንደ እብድ ሰው ነው! እንዲያውም ልክ ኢዩን ይመስላል!” ሲል ተናገረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰላዩም “ደረሰባቸው፤ ነገር ግን አልተመለሰም፤ በችኮላ ይሄዳልና አካሄዱ እንደ ናሜሲ ልጅ እንደ ኢዩ አካሄድ ነው፤” ብሎ ነገረው። |
ዘበኛውም፥ “የፊተኛው ሩጫ እንደ ሳዶቅ ልጅ እንደ አኪማሖስ ሩጫ ይመስላል” አለ፤ “ንጉሡም፦ እርሱ መልካም ሰው ነው፤ መልካምም ወሬ ያመጣል” አለ።
ከአዛሄልም ሰይፍ የሚያመልጠውን ሁሉ ኢዩ ይገድለዋል፤ ከኢዩም ሰይፍ የሚያመልጠውን ሁሉ ኤልሳዕ ይገድለዋል።
“ከእኔ ጋር ና፥ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔርም እንደምቀና ታያለህ” አለው። ከእርሱም ጋር በሰረገላው አስቀመጠው።
ሁለተኛውንም ፈረሰኛ ሰደደ፤ ወደ እነርሱም ደርሶ ንጉሡ እንዲህ ይላል፥ “ሰላም ነውን?” አላቸው። ኢዩም፥ “አንተ ከሰላም ጋር ምን አለህ? ወደ ኋላዬ ተመልሰህ ተከተለኝ” አለ።
በዚያም በደረስህ ጊዜ የናሜሲን ልጅ የኢዮሣፍጥን ልጅ ኢዩን ታገኘዋለህ፤ ገብተህም ከወንድሞቹ መካከል አስነሣው፤ ወደ ጓዳም አግባው።
አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምትችለውን ሁሉ እንደ ኀይልህ አድርግ።
እነሆ፥ ፍሙን በወናፍ እንደሚያናፋ፥ ለሥራውም መሣሪያ እንደሚያወጣ ብረት ሠሪ የፈጠርሁሽ አይደለም፤ እኔ ግን ለመልካም ፈጠርሁሽ እንጂ ለጥፋት አይደለም።