Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 54:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እነሆ፥ ፍሙን በወ​ናፍ እን​ደ​ሚ​ያ​ናፋ፥ ለሥ​ራ​ውም መሣ​ሪያ እን​ደ​ሚ​ያ​ወጣ ብረት ሠሪ የፈ​ጠ​ር​ሁሽ አይ​ደ​ለም፤ እኔ ግን ለመ​ል​ካም ፈጠ​ር​ሁሽ እንጂ ለጥ​ፋት አይ​ደ​ለም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 “እነሆ፤ የከሰሉ ፍም እንዲቀጣጠል የሚያራግበውን፣ የጦር መሣሪያ የሚያበጀውን፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያውን የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤ ጥፋት እንዲያደርስም የፈጠርሁ እኔ ነኝ አጥፊውንም የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እነሆ፥ ፍሙን በወናፍ የሚያናፋ ለሥራውም መሣሪያ የሚያወጣ አንጥረኛን የፈጠርኩ እኔ ነኝ፤ የሚያፈርሰውንም እንዲያጠፋ ፈጥሬአለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 “እነሆ፥ በወናፉ ፍሙን የሚያናፋውን ብረት አቅላጭ የፈጠርኩ እኔ ነኝ፤ እርሱም መሣሪያውን የሚሠራው ለየተሠራለት ዓላማ እንዲውል ለማድረግ ነው፤ ያጠፋ ዘንድ አጥፊውን የፈጠርኩ እኔ ነኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እነሆ፥ ፍሙን በወናፍ የሚያናፋ ለሥራውም መሣሪያ የሚያወጣ ብረት ሠሪን እኔ ፈጥሬአለሁ፥ የሚያፈርሰውንም እንዲያጠፋ ፈጥሬአለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 54:16
14 Referencias Cruzadas  

በልቡ የታበየ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነው። በዐመፃ እጅን በእጅ የሚመታ አይነጻም።


ነገር ግን ኀይ​ሌን እገ​ል​ጥ​ብህ ዘንድ፥ ስሜም በም​ድር ሁሉ ላይ ይነ​ገር ዘንድ ስለ​ዚህ ጠበ​ቅ​ሁህ።


ከም​ሥ​ራ​ቅና ከሩቅ ሀገር ስለ መከ​ር​ሁት ምክር ዎፍን እጠ​ራ​ለሁ፤ ተና​ገ​ርሁ፤ አመ​ጣ​ሁም፤ ፈጠ​ርሁ፤ አደ​ረ​ግ​ሁም፤ አመ​ጣ​ሁት፤ መን​ገ​ዱ​ንም አቀ​ና​ሁ​ለት።


“በውኑ መጥ​ረ​ቢያ በሚ​ቈ​ር​ጥ​በት ሰው ላይ ይነ​ሣ​ልን? ወይስ መጋዝ በሚ​ስ​በው ሰው ላይ ይጓ​ደ​ዳ​ልን? ይህም ዘንግ በሚ​መ​ቱ​በት ላይ እንደ መነ​ሣት፥ በት​ርም ዕን​ጨት አይ​ደ​ለ​ሁም እንደ ማለት ነው።”


“እኔ ጥንት የሠ​ራ​ሁ​ትን አል​ሰ​ማ​ህ​ምን? እኔ በቀ​ድሞ ዘመን እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ሁት፥ አሁ​ንም አሕ​ዛ​ብን በም​ሽ​ጎ​ቻ​ቸው፥ በጽኑ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም ያጠፉ ዘንድ አዘ​ዝሁ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ከሰ​ማይ ካል​ተ​ሰ​ጠህ በቀር በእኔ ላይ አን​ዳች ሥል​ጣን የለ​ህም፤ ስለ​ዚህ ለአ​ንተ አሳ​ልፎ የሰ​ጠኝ ሰው ታላቅ ኀጢ​ኣት አለ​በት” አለው።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም፥ “ዕብ​ራ​ው​ያን ሰይ​ፍና ጦር እን​ዳ​ይ​ሠሩ” ብለው ነበ​ርና በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር ሁሉ ብረት ሠሪ አል​ተ​ገ​ኘም።


እነሆ፥ መጻ​ተ​ኞች በእኔ ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ፤ በአ​ን​ቺም ይማ​ጸ​ናሉ።


በአ​ንቺ ላይ የተ​ሠራ መሣ​ሪያ ሁሉ እን​ዲ​ከ​ና​ወን አላ​ደ​ር​ግም፤ በአ​ንቺ ላይ ለፍ​ርድ የሚ​ነ​ሣ​ውን ድምፅ ሁሉ ታጠ​ፊ​ያ​ለሽ፤ ጠላ​ቶ​ች​ሽም ሁሉ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ርስት አላ​ቸው፤ ጻድ​ቃ​ኔም ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግዚአብሔርም አራት ጠራቢዎች አሳየኝ።


ዓይኖቼንም አነሣሁ፣ እነሆም፥ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ አንድ ሰውን አየሁ።


ሩጥ፥ ይህንም ጕልማሳ እንዲህ በለው፦ ኢየሩሳሌም በውስጥዋ ካሉት ሰዎችና እንስሶች ብዛት የተነሣ ቅጥር እንደሌላቸው መንደሮች ሆና ትኖራለች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios