La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 6:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከዚ​ያም በኋላ የሶ​ርያ ንጉሥ ወልደ አዴር ሠራ​ዊ​ቱን ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ ወጥ​ቶም ሰማ​ር​ያን ከበ​ባት፤ በዚ​ያም ተቀ​መጠ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከጥቂት ጊዜ በኋላም የሶርያ ንጉሥ ቤን ሃዳድ ሰራዊቱን ሁሉ ሰበሰበ፤ ወጥቶም ሰማርያን ከበባት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከጥቂት ጊዜ በኋላ የሶርያ ንጉሥ ቤንሀዳድ መላ ሠራዊቱን በእስራኤል ላይ በማዝመት፥ የሰማርያን ከተማ ከበበ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከጥቂት ጊዜ በኋላ የሶርያ ንጉሥ ቤንሀዳድ መላ ሠራዊቱን በእስራኤል ላይ በማዝመት፥ የሰማርያን ከተማ ከበበ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከዚያም በኋላ የሶርያ ንጉሥ ቤንሀዳድ ሠራዊቱን ሁሉ ሰበሰበ፤ ወጥቶም ሰማርያን ከበባት።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 6:24
12 Referencias Cruzadas  

ለኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው ለና​ቡቴ በሰ​ማ​ርያ ንጉሥ በአ​ክ​ዓብ ቤት አጠ​ገብ የወ​ይን ቦታ ነበ​ረው።


የሶ​ር​ያም ንጉሥ ሠላሳ ሁለ​ቱን የሰ​ረ​ገ​ሎች አለ​ቆች፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በቀር፥ ታናሽ ቢሆን ወይም ታላቅ ከማ​ና​ቸ​ውም ጋር አትዋጉ” ብሎ አዝዞ ነበር።


የአ​ሦ​ርም ንጉሥ በም​ድር ሁሉ ላይ ወጣ፤ ወደ ሰማ​ር​ያም ወጥቶ ሦስት ዓመት ከበ​ባት።


ሕዝ​ቅ​ያስ በነ​ገሠ በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የኤላ ልጅ ሆሴዕ በነ​ገሠ በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት፥ የአ​ሦር ንጉሥ ስል​ም​ና​ሶር ወደ ሰማ​ርያ ወጣ፤ ከበ​ባ​ትም።


ሴዴ​ቅ​ያ​ስም በነ​ገሠ በዘ​ጠ​ነ​ኛው ዓመት በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ከሠ​ራ​ዊቱ ሁሉ ጋር ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጥቶ ሰፈ​ረ​ባት፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ዕርድ ሠራ​ባት።


በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ራብ ጸንቶ ነበ​ርና ለሀ​ገሩ ሰዎች እህል ታጣ።


የሶ​ር​ያም ንጉሥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ይዋጋ ነበር፤ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ጋር ተማ​ክሮ፥ “በዚህ ስውር ቦታ ተደ​ብ​ቀን እና​ድ​ራ​ለን።” አላ​ቸው።


ወደ ከተማ ብን​ገባ ራብ በከ​ተማ አለና፥ በዚያ እን​ሞ​ታ​ለን፤ በዚ​ህም ብን​ቀ​መጥ እን​ሞ​ታ​ለን። እን​ግ​ዲህ ኑ፥ ወደ ሶር​ያ​ው​ያን ሰፈር እን​ሂድ፤ በሕ​ይ​ወት ቢያ​ኖ​ሩን እን​ኖ​ራ​ለን፤ ቢገ​ድ​ሉ​ንም እን​ሞ​ታ​ለን” ተባ​ባሉ።


ኤል​ሳ​ዕም ወደ ደማ​ስቆ ሄደ፤ የሶ​ር​ያም ንጉሥ ወልደ አዴር ታምሞ ነበር፤ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ​ዚህ መጥ​ቶ​አል” ብለ​ውም ነገ​ሩት።


ታናሽ ከተማ ነበ​ረች፥ ጥቂ​ቶች ሰዎ​ችም ነበ​ሩ​ባት፤ ታላቅ ንጉ​ሥም መጣ​ባት፥ ከበ​ባ​ትም፥ ታላቅ ግን​ብ​ንም ሠራ​ባት።


በአ​ዛ​ሄል ቤት ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የወ​ልደ አዴ​ር​ንም መሠ​ረ​ቶች ትበ​ላ​ለች።


በሀ​ገ​ርህ ሁሉ ያሉ፥ ትታ​መ​ን​ባ​ቸው የነ​በሩ፥ የረ​ዘሙ፥ የጸ​ኑም ቅጥ​ሮች እስ​ኪ​ፈ​ርሱ ድረስ፥ በከ​ተ​ሞ​ችህ ሁሉ ያጠ​ፋ​ሃል፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ጠህ ምድር ሁሉ፥ በደ​ጆች ሁሉ ያስ​ጨ​ን​ቅ​ሃል።