ዮአክስም በነገሠ ጊዜ ሃያ ሦስት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወር ነገሠ። እናቱም አሚጣል ትባል ነበር፥ እርስዋም የሎብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።
2 ነገሥት 24:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴዴቅያስም በነገሠ ጊዜ ሃያ አንድ ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም አሚጣል የተባለች የሎብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴዴቅያስ ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ አንድ ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ። የእናቱም ስም አሚጣል ነበረ፤ እርሷም የልብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴዴቅያስ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሀያ አንድ ዓመት ነበር፤ መኖርያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ፤ እናቱም ሐሙጣል ተብላ የምትጠራ የልብና ከተማ ተወላጅ የነበረው የኤርምያስ ልጅ ነበረች፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴዴቅያስ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ኻያ አንድ ዓመት ነበር፤ መኖርያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ፤ እናቱም ሐሙጣል ተብላ የምትጠራ የልብና ከተማ ተወላጅ የነበረው የኤርምያስ ልጅ ነበረች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴዴቅያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አንድ ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም አሚጣል የተባለች የልብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች። |
ዮአክስም በነገሠ ጊዜ ሃያ ሦስት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወር ነገሠ። እናቱም አሚጣል ትባል ነበር፥ እርስዋም የሎብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።
የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ የመልክያን ልጅ ጳስኮርንና የካህኑን የመዕሴይን ልጅ ሶፎንያስን ወደ ኤርምያስ በላከ ጊዜ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦ እንዲህም አለ፦
በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም መንግሥት መጀመሪያ ይህ ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ።
ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ፤ በዚያ ዓመት፥ በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ መንግሥት መጀመሪያ፥ በአራተኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ሐሰተኛው ነቢይ የገባዖን ሰው የዓዙር ልጅ ሐናንያ በእግዚአብሔር ቤት በካህናትና በሕዝብ ሁሉ ፊት እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በይሁዳ ያነገሠው የኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ በኢዮአቄም ልጅ በኢኮንያን ፋንታ ነገሠ።
በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ በመጀመሪያው ዓመተ መንግሥት ስለ ኤላም ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።