የአሦርም ንጉሥ ተርታንንና ራፌስን ራፋስቂስንም ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም ላካቸው። ወጥተውም ወደ ኢየሩሳሌም ደረሱ፤ በአጣቢውም እርሻ መንገድ ባለችው በላዪኛዪቱ ኩሬ መስኖ አጠገብ ቆሙ።
2 ነገሥት 19:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢሳይያስም አላቸው፥ “ለጌታችሁ እንዲህ በሉት፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአሦር ንጉሥ ብላቴኖች ስለ ተሳደቡት፥ ስለ ሰማኸው ቃል አትፍራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢሳይያስም እንዲህ አላቸው፤ “ጌታችሁን እንዲህ በሉት፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የአሦር ንጉሥ ባሪያዎች እኔን ስለ ሰደቡኝ፣ በሰማኸው ቃል አትሸበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢሳይያስ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብላችሁ ለጌታችሁ ንገሩት አላቸው፤ ‘የአሦር ንጉሥ አገልጋዮች ሲሰድቡኝ ስለ ሰማችሁት ቃል አትፍሩአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢሳይያስ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብላችሁ ለጌታችሁ ንገሩት አላቸው፤ ‘የአሦር ንጉሥ አገልጋዮች ሲሰድቡኝ ስለ ሰማችሁት ቃል አትፍሩአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢሳያስም “ለጌታችሁ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘የአሦር ንጉሥ ባሪያዎች ስለ ሰደቡኝ፥ ስለ ሰማኸው ቃል አትፍራ። |
የአሦርም ንጉሥ ተርታንንና ራፌስን ራፋስቂስንም ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም ላካቸው። ወጥተውም ወደ ኢየሩሳሌም ደረሱ፤ በአጣቢውም እርሻ መንገድ ባለችው በላዪኛዪቱ ኩሬ መስኖ አጠገብ ቆሙ።
ሕዝቅያስም፦ እግዚአብሔር በእርግጥ ያድነናል፤ ይህችንም ከተማ የአሦር ንጉሥ ሊይዛት አይችልም እያለ በእግዚአብሔር እንድትታመኑ አያድርጋችሁ።
የተገዳደርኸው፥ የሰደብኸውስ ማን ነው? ቃልህንስ ከፍ ከፍ ያደረግኸው፥ ዐይንህንም ወደ ላይ ያነሣኸው በማን ላይ ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ ነው።
እንዲህም አለ፥ “ይሁዳ ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ፥ አንተም ንጉሡ ኢዮሣፍጥ! ስሙ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላችኋል፦ ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው እንጂ የእናንተ አይደለምና ከዚህ ታላቅ ወገን የተነሣ አትፍሩ፤ አትደንግጡም።
እናንተ የምቷጉ አይደላችሁም፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ተሰለፉ፤ ዝም ብላችሁ ቁሙ፤ የሚሆነውንም የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ፤ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ነውና አትፍሩ፤ አትደንግጡም፤ ነገም ውጡባቸው።”
ሙሴም ለሕዝቡ፥ “አትፍሩ፤ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘለዓለም አታዩአቸውምና ቁሙ፤ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ።
ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በጽዮን የምትኖር ሕዝቤ ሆይ፥ ከአሦር የተነሣ አትፍራ፤ በበትር ይመቱሃልና፥ የግብፅንም መንገድ ታይ ዘንድ መቅሠፍቴን አመጣብሃለሁና።
እንዲህም አላቸው፥ “ልመናችሁን በፊቱ አቀርብ ዘንድ ወደ እርሱ የላካችሁኝ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
ከእናንተም አምስቱ መቶውን ያሳድዳሉ፤ መቶውም ዐሥሩን ሺህ ያሳድዳሉ፤ ጠላቶቻችሁም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።
“ጠላቶችህን ለመውጋት በወጣህ ጊዜ፥ ፈረሶችንና ፈረሰኞችን ሕዝቡንም ከአንተ ይልቅ በዝተው ባየህ ጊዜ፥ ከግብፅ ሀገር ያወጣህ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና አትፍራቸው።
እግዚአብሔርም ኢያሱን፥ “በእስራኤል ፊት ይሞቱ ዘንድ ነገ በዚህ ጊዜ ሁሉን በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና አትፍራቸው፤ የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ትቈርጣለህ፤ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት ታቃጥላለህ” አለው።