2 ነገሥት 17:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች በአምላካቸው በእግዚአብሔር ላይ ቅን ያልሆነን ነገር በስውር አደረጉ፤ በከተሞቻቸውም ሁሉ ከዘበኞች ግንብ ጀምሮ እስከ ተመሸገች ከተማ ድረስ በከፍታዎች ላይ መስገጃዎችን ሠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን በአምላካቸው በእግዚአብሔር ላይ ትክክል ያልሆነ ነገር በስውር አደረጉ፤ ከቃፊር መጠባበቂያ ማማ አንሥቶ እስከ ተመሸገው ከተማ ባሉት መኖሪያዎቻቸው ሁሉ በሚገኙት ኰረብቶች ላይ ማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤላውያን አምላካቸው እግዚአብሔር የሚጠላውን ነገር ሁሉ አደረጉ፤ ከዘብ ጠባቂዎች ማማ አንሥቶ እስከ ትልቅ ከተማ ድረስ በገጠር ከተሞቻቸው ሁሉ በየኰረብታዎቹ የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን አምላካቸው እግዚአብሔር የሚጠላውን ነገር ሁሉ አደረጉ፤ ከዘብ ጠባቂዎች ማማ አንሥቶ እስከ ትልቅ ከተማ ድረስ በገጠር ከተሞቻቸው ሁሉ በየኰረብታዎቹ የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች በአምላካቸው በእግዚአብሔር ላይ ቅን ያልሆነውን ንገር በስውር አደረጉ፤ በከተሞቻቸውም ሁሉ ከዘበኞች ግንብ ጀምሮ እስከ ተመሸገች ከተማ ድረስ በከፍታዎቹ ላይ መስገጃዎችን ሠሩ። |
ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከእግዚአብሔር ለሚሰውሩ ወዮላቸው! ሥራቸውንም በጨለማ ውስጥ አድርገው፥ “ማን ያየናል? ወይስ ማን ያውቀናል?” ለሚሉ ወዮላቸው!
እሰጣቸውም ዘንድ እጄን ወደ አነሣሁላቸው ምድር አገባኋቸው፤ ከፍ ያለውን ኮረብታ ሁሉ፥ ቅጠላማውንም ዛፍ ሁሉ አዩ፤ በዚያም ለጣዖቶቻቸው መሥዋዕታቸውን ሠዉ፤ በዚያም የሚያስቈጣኝን፤ ቍርባናቸውን አቀረቡ፤ በዚያም ደግሞ ጣፋጩን ሽታቸውን አደረጉ፤ በዚያም የመጠጥ ቍርባናቸውን አፈሰሱ።
እርሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች በስውር እያንዳንዱ በሥዕሉ ቤት የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱ እግዚአብሔር አያየንም፤ እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቶአታል ይላሉና” አለኝ።
“የአባትህ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም አብራህ የምትተኛ ሚስትህ ወይም እንደ ነፍስህ ያለ ወዳጅህ በስውር፦ ና፥ ሄደን አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ ቢያስትህ፥
“በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ የሠራተኛ እጅ ሥራን፥ የተቀረፀ ወይም ቀልጦ የተሠራ ምስልን የሚያደርግ፥ በስውርም የሚያቆመው ሰው ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ መልሰው አሜን ይላሉ።
ሰዎችም እንዲህ ይላሉ፦ የአባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ከግብፅ ምድር ባወጣቸው ጊዜ ከአባቶቻቸው ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን ስለተዉ፥