2 ነገሥት 15:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጋዲም ልጅ ምናሔም ከቴርሳላቅ ወጥቶ ወደ ሰማርያ ሄደ፤ በሰማርያም የኢያቢስን ልጅ ሴሎምን መታ፤ ገደለውም፤ በእርሱም ፋንታ ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጋዲ ልጅ ምናሔም ከቴርሳ ወጥቶ ወደ ሰማርያ በመሄድ አደጋ ጥሎ የኢያቤስን ልጅ ሰሎምን ገደለው፤ ከዚያም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምናሔም ተብሎ የሚጠራው የጋዲ ልጅ ከቲርጻ ተነሥቶ ወደ ሰማርያ ሄደ፤ ሻሉምንም ገድሎ በእርሱ እግር ነገሠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምናሔም ተብሎ የሚጠራው የጋዲ ልጅ ከቲርጻ ተነሥቶ ወደ ሰማርያ ሄደ፤ ሻሉምንም ገድሎ በእርሱ እግር ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጋዲም ልጅ ምናሔም ከቴርሳ ወጥቶ ወደ ሰማርያ መጣ፤ በሰማርያም የኢያቤስን ልጅ ሰሎምን መታ፤ ገደለውም፤ በእርሱም ፋንታ ነገሠ። |
በይሁዳም ንጉሥ በአሳ በሦስተኛው ዓመት የአኪያ ልጅ ባኦስ በእስራኤል ሁሉ ላይ በቴርሣ ንጉሥ ሆኖ ሃያ አራት ዓመት ነገሠ።
በይሁዳም ንጉሥ በአሳ በሃያ ዘጠነኛው ዓመት ዘምሪ በቴርሳ ሰባት ቀን ነገሠ። የእስራኤል ሠራዊት ግን በፍልስጥኤም ሀገር በገባቶን ሰፍረው ነበር።