2 ነገሥት 15:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢያቢስም ልጅ ሴሎም፤ ሌሎችም ከዱት፤ በይብልዓም መትተው ገደሉት፤ በእርሱም ፋንታ ሴሎም ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኢያቤስ ልጅ ሰሎም በዘካርያስ ላይ አሤረበት፤ በሕዝቡ ፊት አደጋ ጥሎ ገደለው፤ በእግሩም ተተክቶ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሻሉም ተብሎ የሚጠራው የያቤሽ ልጅ ሤራ በማድረግ ዪብለዓም ተብላ በምትጠራው ስፍራ ንጉሥ ዘካርያስን ገድሎ በእርሱ እግር ነገሠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሻሉም ተብሎ የሚጠራው የያቤሽ ልጅ ሤራ በማድረግ ዪብለዓም ተብላ በምትጠራው ስፍራ ንጉሥ ዘካርያስን ገድሎ በእርሱ እግር ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኢያቤስም ልጅ ሰሎም ተማማለበት፤ በይብልዓም መትቶ ገደለው፤ በእርሱም ፋንታ ነገሠ። |
አገልጋዮቹም የኢያሙሃት ልጅ ኢያዜክርና የሳሜር ልጅ ኢያዛብድ መቱት፤ ሞተም፤ በዳዊትም ከተማ ከአባቶቹ ጋር ቀበሩት፤ ልጁም አሜስያስ በፋንታው ነገሠ።
የጋዲም ልጅ ምናሔም ከቴርሳላቅ ወጥቶ ወደ ሰማርያ ሄደ፤ በሰማርያም የኢያቢስን ልጅ ሴሎምን መታ፤ ገደለውም፤ በእርሱም ፋንታ ነገሠ።
የሠራዊቱም አለቃ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ከዳው፤ በሰማርያም በንጉሡ ቤት ግንብ ውስጥ ከአርጎብና ከአርያ ጋር መታው፤ ከእርሱም ጋር ከገለዓዳውያን አምሳ ሰዎች ነበሩ፤ ገደለውም፤ በእርሱም ፋንታ ነገሠ።
በዖዝያንም ልጅ በኢዮአታም በሃያኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በሮሜልዮ ልጅ በፋቁሔ ላይ ዐመፀበት፤ መትቶም ገደለው፤ በእርሱም ፋንታ ነገሠ።
አባቶቹም እንዳደረጉት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ፤ እስራኤልንም ካሳታቸው ከናባጥ ልጅ ከኢዮርብዓም ኀጢአት አልራቀም።
ኢዩም በእጁ ቀስቱን ለጠጠ፤ ኢዮራምንም በጫንቃው መካከል ወጋው ፤ ፍላጻውም በልቡ አለፈ፤ ወደ ሰረገላውም ውስጥ በጕልበቱ ላይ ወደቀ።
ሁሉም እንደ ምድጃ ግለዋል፤ ፈራጆቻቸውንም በሉ፤ ነገሥታቶቻቸውም ሁሉ ወደቁ፤ ከእነርሱም መካከል የሚጠራኝ የለም።
ራሳቸውን አነገሡ፤ ከእኔም ዘንድ አይደለም፤ አለቆችንም አደረጉ፤ እኔም አላወቅሁም፤ ለጥፋታቸውም ከብራቸውና ከወርቃቸው ጣዖታትን ለራሳቸው አደረጉ።
መሳቂያ የሆኑ የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፤ የእስራኤልም መቅደሶች ባድማ ይሆናሉ፤ በኢዮርብዓምም ቤት ላይ በሰይፍ እነሣለሁ” አለ።