ዕድሜህም በተፈጸመ ጊዜ፤ ከአባቶችህም ጋር ባንቀላፋህ ጊዜ፥ ከወገብህ የሚወጣውን ዘርህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ፤ መንግሥቱንም አዘጋጃለሁ ።
2 ነገሥት 10:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዩም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በሰማርያም ቀበሩት። በፋንታውም ልጁ ኢዩአካዝ ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዩ ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ በሰማርያ ቀበሩት። ልጁ ኢዮአካዝም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ ኢዩ ሞተ፤ በሰማርያም ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ኢዮአካዝ ነገሠ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ኢዩ ሞተ፤ በሰማርያም ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ኢዮአካዝ ነገሠ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዩም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በሰማርያም ቀበሩት። በፋንታውም ልጁ ኢዮአካዝ ነገሠ። |
ዕድሜህም በተፈጸመ ጊዜ፤ ከአባቶችህም ጋር ባንቀላፋህ ጊዜ፥ ከወገብህ የሚወጣውን ዘርህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ፤ መንግሥቱንም አዘጋጃለሁ ።
እግዚአብሔርም ኢዩን፥ “በፊቴ ቅን ነገር አድርገሃልና፥ በልቤም ያለውን ሁሉ በአክአብ ቤት ላይ አድርገሃልና ልጆችህ እስከ አራት ትውልድ ድረስ በእስራኤል ዙፋን ላይ ይቀመጣሉ” አለው።
የቀረውም የኢዩ ነገር፥ የሠራውም ሥራ ሁሉ፥ ኀይሉም ሁሉ፥ የገደለውም ሁሉ እነሆ፥ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?
በይሁዳ ንጉሥ በአካዝያስ ልጅ በኢዮአስ በሃያ ሦስተኛው ዓመት የኢዩ ልጅ ኢዮአካዝ በሰማርያ ነገሠ፤ ዐሥራ ሰባት ዓመትም ነገሠ።