በቤቴል ባለው መሠዊያ ላይ፥ በሰማርያም ከተሞች ውስጥ ባሉት በኮረብታዎቹ መስገጃዎች ላይ በእግዚአብሔር ቃል የተናገረው ነገር በእውነት ይደርሳልና።”
2 ነገሥት 10:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአክአብም በሰማርያ ሰባ ልጆች ነበሩት፤ ኢዩም ደብዳቤ ጽፎ፥ የአክአብን ልጆች ለሚያሳድጉ፥ ለሰማርያ አለቆችና ሽማግሌዎች ወደ ሰማርያ ላከ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ አክዓብ በሰማርያ ሰባ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ስለዚህ ኢዩ ደብዳቤ ጽፎ ለኢይዝራኤል ሹማምት፣ ለሽማግሌዎችና የአክዓብን ልጆች ለሚያሳድጉ ሞግዚቶች ወደ ሰማርያ ላከ፤ መልእክቱም እንዲህ የሚል ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብዛታቸው ሰባ የሚሆን የአክዓብ ልጆች በሰማርያ ከተማ ይኖሩ ነበር፤ ኢዩ ደብዳቤ ጽፎ የደብዳቤውን አንዳንድ ቅጂ ለከተማይቱ ገዢዎች፥ ለታወቁ የአገር ሽማግሌዎችና የአክዓብን ተወላጆች ለሚያሳድጉ ሞግዚቶች ሁሉ ላከ፤ የደብዳቤውም ቃል፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዛታቸው ሰባ የሚሆን የአክዓብ ልጆች በሰማርያ ከተማ ይኖሩ ነበር፤ ኢዩ ደብዳቤ ጽፎ የደብዳቤውን አንዳንድ ቅጂ ለከተማይቱ ገዢዎች፥ ለታወቁ የአገር ሽማግሌዎችና የአክዓብን ተወላጆች ለሚያሳድጉ ሞግዚቶች ሁሉ ላከ፤ የደብዳቤውም ቃል፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአክዓብም በሰማርያ ሰባ ልጆች ነበሩት፤ ኢዩም ደብዳቤ ጻፈ፤ የአክዓብን ልጆች ለሚያሳድጉ ለሰማርያ ታላላቆችና ሽማግሌዎች |
በቤቴል ባለው መሠዊያ ላይ፥ በሰማርያም ከተሞች ውስጥ ባሉት በኮረብታዎቹ መስገጃዎች ላይ በእግዚአብሔር ቃል የተናገረው ነገር በእውነት ይደርሳልና።”
ዘንበሪም ከዚያች ተራራ ባለቤት ከሴሜር በሁለት መክሊት ብር የሳምሮንን ተራራ ገዛ፤ በተራራውም ላይ ከተማ ሠራ፤ የሠራትንም ከተማ በተራራው ባለቤት በሳምር ስም ሰማርያ ብሎ ጠራት።
ዘንበሪም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በሰማርያም ቀበሩት፤ ልጁም አክአብ በፋንታው ነገሠ። 28 ‘ሀ’ ዘንበሪም ዐሥራ አንድ ዓመት ሲሆነው የአሳ ልጅ ኢዮሳፍጥ ነገሠ። በነገሠም ጊዜ ሠላሳ አምስት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሃያ አምስት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ጋዙባ የምትባል የሴላህ ልጅ ነበረች። 28 ‘ለ’ በአባቱም በአሳ መንገድ ሄደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ጽድቅን ያደርግ ዘንድ ከእርስዋ ፈቀቅ አላለም። በተራሮች የነበሩትንም አማልክት አላስወገደም፤ ሕዝቡም በተራሮቹ ይሠዉላቸውና ያጥኑላቸው ነበረ። 28 ‘ሐ’ ኢዮሳፍጥም ከእስራኤል ንጉሥ ጋር የሠራው፥ የተዋጋውና ያደረገው ኀይል ሁሉ እነሆ፥ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ ነው። 28 ‘መ’ በአባቱም በአሳ ዘመን የነበረውን ርኵሰት ሁሉ ከምድር አስወገደ። በኤዶምም ንጉሥ አልነበረም። 28 ‘ሠ’ ንጉሥ ኢዮሳፍጥም ወርቅና ብርን ሊያመጡለት ወደ አፌር ይልክ ዘንድ በተርሴስ መርከብ አሠራ፤ በጋስዮንጋቤር የነበረችው መርከብ ተሰብራለችና አልሄደችም። 28 ‘ረ’ የእስራኤልም ንጉሥ አካዝያስ ኢዮሳፍጥን፥ “አገልጋዮችህንና አገልጋዮቼን በመርከብ እንላክ” አለው። ኢዮሳፍጥም እንቢ አለ። 28 ‘ሰ’ ኢዮሳፍጥም እንደ አባቶቹ አንቀላፋ። በዳዊትም ከተማ ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ። በእርሱም ፋንታ ልጁ ኢዮራም ነገሠ።
እነዚህም በእነዚያ ትይዩ ሰባት ቀን ያህል ሰፈሩ፤ በሰባተኛውም ቀን ተጋጠሙ፤ የእስራኤልም ልጆች ከሶርያውያን በአንድ ቀን መቶ ሺህ እግረኛ ገደሉ።
እመቤቷንም፥ “ጌታዬ በሰማርያ ወደሚኖረው ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ነቢዩ ይሄድ ዘንድ በተገባው ነበር፤ ከለምጹም በፈወሰው ነበር” አለቻት።
አካዝያስንም ፈለገው፤ በሰማርያም እየታከመ ሳለ አገኙት፤ ወደ ኢዩም አመጡት፤ እርሱም ገደለው፦ እነርሱም፥ “በፍጹም ልብ እግዚአብሔርን የፈለገው የኢዮሣፍጥ ልጅ ነው” ብለው ቀበሩት። ከአካዝያስም ቤት ማንም መንግሥትን ይይዝ ዘንድ የሚችል አልነበረም።
እግዚአብሔርም፥ “ከጥቂት ዘመን በኋላ የኢይዝራኤልን ደም በይሁዳ ቤት ላይ እበቀላለሁና፥ ከእስራኤልም ቤት መንግሥትን እሽራለሁና ስሙን ኢይዝራኤል ብለህ ጥራው፤
አንተ ለአባቶቻቸው ወደ ማልህላቸው ምድር አደርሳቸው ዘንድ፦ ሞግዚት የሚጠባውን ልጅ እንድታቅፍ በብትህ እቀፋቸው የምትለኝ፥ በውኑ ይህን ሕዝብ ሁሉ እኔ ፀነስሁትን? ወይስ ወለድሁትን?
“አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ በሀገርህ ደጅ ሁሉ በየነገዶችህ ፈራጆችንና መባውን የሚጽፉትን ሹሙ፤ ለሕዝቡም ቅን ፍርድን ይፍረዱ።
በሠላሳ ሁለት የአህያ ግልገሎች ይቀመጡ የነበሩ ሠላሳ ሁለት ልጆችም ነበሩት፤ ለእነርሱም እስከ ዛሬ ድረስ የኢያዕር መንደሮች የተባሉ በገለዓድ ምድር ያሉ ሠላሳ ሁለት ከተሞች ነበሩአቸው።
አርባም ልጆች፥ ሠላሳም የልጅ ልጆች ተወለዱለት፤ በሰባም የአህያ ግልገሎች ላይ ይቀመጡ ነበር። እስራኤልንም ስምንት ዓመት ገዛ።