እንዲሁም የስምዖን ባልንጀራዎች የነበሩ የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስ ተደነቁ፤ ጌታችን ኢየሱስም ስምዖንን፥ “አትፍራ፤ ከእንግዲህ ወዲህስ ሰውን ታጠምዳለህ” አለው።
2 ቆሮንቶስ 8:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቲቶም ቢሆን፥ ስለ እናንተ አብሮኝ የሚሠራ ጓደኛዬ ነው፥ ወንድሞቻችንም ቢሆኑ፥ ለእግዚአብሔር ክብር የአብያተ ክርስቲያናት ሐዋርያት ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ቲቶ የሚጠይቅ ቢኖር፣ እርሱ እናንተን ለማገልገል ዐብሮኝ የሚሠራ ባልደረባዬ ነው፤ ስለ ወንድሞቻችንም የሚጠይቅ ቢኖር እነርሱ የአብያተ ክርስቲያናት ተወካዮችና የክርስቶስ ክብር ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ቲቶ የሚጠይቅ ቢኖር፥ እናንተን ለማገልገል አብሮኝ የሚሠራ ባልንጀራዬ ነው፤ ስለ ወንድሞቻችን የሚጠይቅ ቢኖር፥ የአብያተ ክርስቲያናት መልእክተኞችና የክርስቶስ ክብር ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ቲቶ ማወቅ ቢያስፈልግ እናንተን ለመርዳት አብሮኝ የሚሠራ የሥራ ጓደኛዬ ነው፤ ከእርሱ ጋር ስለሚመጡት ስለ ሌሎች ወንድሞች የሆነ እንደ ሆነ እነርሱ የአብያተ ክርስቲያን ተወካዮች ለክርስቶስ ክብር የቆሙ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ቲቶ የሚጠይቅ ቢኖር ስለ እናንተ አብሮኝ የሚሠራ ባልንጀራዬ ነው፤ ስለ ወንድሞቻችን የሚጠይቅ ቢኖርም የአብያተ ክርስቲያናት መልእክተኞችና የክርስቶስ ክብር ናቸው። |
እንዲሁም የስምዖን ባልንጀራዎች የነበሩ የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስ ተደነቁ፤ ጌታችን ኢየሱስም ስምዖንን፥ “አትፍራ፤ ከእንግዲህ ወዲህስ ሰውን ታጠምዳለህ” አለው።
መጥተውም ይረዱአቸው ዘንድ በሌላ ታንኳ የነበሩትን ባልንጀሮቻቸውን ጠሩ፤ መጥተውም እስኪጠልቁ ድረስ ሁለቱን ታንኳዎች ሞሉ።
ወንድ በሚጸልይበት ጊዜ ሊከናነብ አይገባውም፤ የእግዚአብሔር አርአያውና አምሳሉ ነውና፤ ሴትም ለባልዋ ክብር ናት።
እነሆ ቲቶን ማለድሁት፤ ከእርሱም ጋር ሌላውን ወንድማችንን ላክሁት፤ በውኑ ቲቶ የበደላችሁ በደል አለን? በእርሱ በአደረው መንፈስ የምንመላለስ፥ እርሱም የሄደበትን ፍለጋ የምንከተል አይደለንምን?
ይህም ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ክብርና የእኛን በጎ ፈቃድ ለማሳየት በምናገለግልባት በዚች ጸጋ ከእኛ ጋር አንድ ይሆን ዘንድ በአብያተ ክርስቲያናት ተሾመ።
በብዙ የፈተንነውንና በሁሉም ነገር ትጉህ ሆኖ ያገኘነውን አሁንም በእናንተ እጅግ ስለሚታመን ከፊት ይልቅ እጅግ ትጉ የሚሆነውን ወንድማችንን ከእነርሱ ጋር እንልካለን።
አሁንም አብሮኝ የሚሠራውን ወንድማችንን አፍሮዲጡን ወደ እናንተ ልልከው አስቤአለሁ፤ እርሱም የክርስቶስ ሎሌ ነው፤ ለእናንተም መምህራችሁ ነው፤ ለእኔም ለችግሬ ጊዜ መልእክተኛዬ ነው።
ወንድሜና አጋዤ ስትሪካ ሆይ፥ እንድትረዳቸው አንተንም እለምንሃለሁ፤ ወንጌልን በማስተማር ከቀሌምንጦስና ሥራቸው ከተባበረ፥ ስማቸውም በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፈላቸው ከወንድሞቻችንም ሁሉ ጋር ከእኔም ጋር ደክመዋልና።
ስለ እናንተ የሚላክ በክርስቶስ የታመነ፥ የእኛም ወንድማችንና አገልጋያችን ከሚሆን ከኤጳፍራስ ተምራችኋል።
ነገር ግን እንደምታውቁት በፊልጵስዩስ አስቀድመን መከራ ተቀብለን ተንገላትተንም፥ በብዙ ገድል የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ እንናገር ዘንድ በአምላካችን ደፈርን።
በሃይማኖት ኅብረት እውነተኛ ልጄ ለሚሆን ለቲቶ፤ ከእግዚአብሔር አብ ከመድኃኒታችንም ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን።