Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ቆሮንቶስ 8:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ስለ ቲቶ ማወቅ ቢያስፈልግ እናንተን ለመርዳት አብሮኝ የሚሠራ የሥራ ጓደኛዬ ነው፤ ከእርሱ ጋር ስለሚመጡት ስለ ሌሎች ወንድሞች የሆነ እንደ ሆነ እነርሱ የአብያተ ክርስቲያን ተወካዮች ለክርስቶስ ክብር የቆሙ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ስለ ቲቶ የሚጠይቅ ቢኖር፣ እርሱ እናንተን ለማገልገል ዐብሮኝ የሚሠራ ባልደረባዬ ነው፤ ስለ ወንድሞቻችንም የሚጠይቅ ቢኖር እነርሱ የአብያተ ክርስቲያናት ተወካዮችና የክርስቶስ ክብር ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ስለ ቲቶ የሚጠይቅ ቢኖር፥ እናንተን ለማገልገል አብሮኝ የሚሠራ ባልንጀራዬ ነው፤ ስለ ወንድሞቻችን የሚጠይቅ ቢኖር፥ የአብያተ ክርስቲያናት መልእክተኞችና የክርስቶስ ክብር ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ቲቶም ቢሆን፥ ስለ እና​ንተ አብ​ሮኝ የሚ​ሠራ ጓደ​ኛዬ ነው፥ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ቢሆኑ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር የአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሐዋ​ር​ያት ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ስለ ቲቶ የሚጠይቅ ቢኖር ስለ እናንተ አብሮኝ የሚሠራ ባልንጀራዬ ነው፤ ስለ ወንድሞቻችን የሚጠይቅ ቢኖርም የአብያተ ክርስቲያናት መልእክተኞችና የክርስቶስ ክብር ናቸው።

Ver Capítulo Copiar




2 ቆሮንቶስ 8:23
20 Referencias Cruzadas  

እንዲሁም የስምዖን ጓደኞች የሆኑት የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስም ተገርመው ነበር። ኢየሱስ ስምዖንን፦ “አይዞህ አትፍራ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሰዎችን የምታጠምድ ትሆናለህ፤” አለው።


ስለዚህ በሌላይቱ ጀልባ ላይ የነበሩት ጓደኞቻቸው መጥተው እንዲያግዙአቸው በጥቅሻ ጠሩአቸው፤ እነርሱም መጥተው ሁለቱ ጀልባዎች ሊሰምጡ ጥቂት እስኪቀራቸው ድረስ በዓሣ ሞሉአቸው።


እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ አገልጋይ ከጌታው አይበልጥም፤ መልእክተኛም ከላኪው አይበልጥም።


ወንድ የእግዚአብሔር መልክና የእግዚአብሔር ክብር የሚገለጥበት ስለ ሆነ ራሱን መከናነብ አይገባውም፤ ሴት ግን የወንድ ክብር ናት።


ቲቶ ወደ እናንተ እንዲመጣ ለመንኩት፤ ያንን ወንድማችንንም ከእርሱ ጋር ላክሁት፤ ታዲያ፥ ቲቶስ ተጠቀመባችሁን? እኔና እርሱ ያገለገልናችሁ በአንድ መንፈስ አልነበረምን? አካሄዳችንስ አንድ አልነበረምን?


ነገር ግን የተዋረዱትን የሚያጽናና አምላክ በቲቶ መምጣት አጽናናን።


እኔ ለእናንተ የማስበውን ያኽል ቲቶም ለእናንተ ከልቡ እንዲያስብ ያደረገ አምላክ ይመስገን።


በወንጌል ስብከቱ በአብያተ ክርስቲያን ሁሉ የተመሰገነውን ወንድም ከእርሱ ጋር እንልካለን።


ከዚህም በላይ ይህ ወንድም እኛ ይህን በጎ ሥራ ለጌታ ክብር ስንፈጽምና ለማገልገል ያለንንም መልካም ፈቃድ ስንገልጥ አብሮን በመሄድ የሥራ ተካፋያችን እንዲሆን በአብያተ ክርስቲያን የተመረጠ ነው።


ብዙ ጊዜ በብዙ መንገድ ተፈትኖ ትጉህ ሆኖ የተገኘውን ወንድማችንን ከነቲቶ ጋር የላክነውም በዚሁ ምክንያት ነው፤ እርሱ በእናንተ ላይ ያለው እምነት ትልቅ ስለ ሆነ አሁን በዚህ ሥራ ለመርዳት ያለው ትጋት ከምንጊዜውም የበለጠ ነው።


ይህን ሥራ አስቀድሞ የጀመረው ቲቶ ስለ ነበረ አሁንም ይህንኑ የልግሥና ሥራችሁን ወደ ፍጻሜ እንዲያደርስ እርሱኑ ለምነነዋል።


እንዲሁም እኔን በሚያስፈልገኝ ሁሉ እንዲረዳኝ ልካችሁት የነበረውን ወንድሜን ኤጳፍሮዲቱስን ወደ እናንተ መላክ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፤ እርሱ ከእኔ ጋር የተሰለፈ ወታደርና የሥራ ጓደኛዬ ሆኖ ሲሠራ የቈየ ነው።


አንተም እዚያ ያለኸው ታማኝ የሥራ ጓደኛዬ እነዚህን ሴቶች እንድትረዳቸው እለምንሃለሁ፤ እነዚህ ሴቶች ከእኔ ጋር ከቀሌምንጦስና ስሞቻቸው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት ከሌሎችም የሥራ ጓደኞቼ ጋር በመሆን ወንጌልን በማዳረስ ረገድ ተጋድለዋል።


ይህንንም በእኛ ምትክ የክርስቶስ ታማኝ አገልጋይ የሆነውና ከእኛም ጋር አብሮን የሚሠራው የተወደደው ኤጳፍራ ነግሮአችኋል።


እናንተ እንደምታውቁት ከዚህ ቀደም በፊልጵስዩስ በነበርንበት ጊዜ መከራና ስድብ ደርሶብናል፤ ነገር ግን ታላቅ ተቃውሞ ቢደርስብንም እንኳ ወንጌሉን ለእናንተ እንድናስተምር አምላካችን ድፍረትን ሰጥቶናል።


ዴማስ ይህን ዓለም ወዶ ተለይቶኛል፤ ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአል፤ ቄርቂስ ወደ ገላትያ፥ ቲቶም ወደ ድልማጥያ ሄደዋል።


የጋራችን በሆነው እምነት በእውነት ልጄ ለሆንከው ለቲቶ፥ ከእግዚአብሔር አብና ከአዳኛችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለአንተ ይሁን።


እንግዲህ እኔን እንደ ወንድም አድርገህ ከቈጠርከኝ ልክ እንደ እኔ አድርገህ ተቀበለው።


እንዲሁም የሥራ ጓደኞቼ የሆኑት ማርቆስ፥ አርስጥሮኮስ፥ ዴማስና፥ ሉቃስ ሰላምታ ያቀርቡልሃል።


የእውነት ሥራ ተካፋዮች እንድንሆን እንደእነዚህ ያሉትን ሰዎች መርዳት አለብን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos