2 ቆሮንቶስ 8:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 በብዙ የፈተንነውንና በሁሉም ነገር ትጉህ ሆኖ ያገኘነውን አሁንም በእናንተ እጅግ ስለሚታመን ከፊት ይልቅ እጅግ ትጉ የሚሆነውን ወንድማችንን ከእነርሱ ጋር እንልካለን። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ደግሞም ብዙ ጊዜ በብዙ መንገድ ተፈትኖ ትጉ ሆኖ የተገኘውን ወንድማችንን ከእነርሱ ጋራ ልከነዋል፤ አሁንም በእናንተ እጅግ ከመታመኑ የተነሣ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ እየተጋ ነው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 በብዙ ነገር ተፈትኖና በብዙ ጉዳዮች ትጉህ ሆኖ ያገኘነውን ወንድማችንን ከእነርሱ ጋር ልከነዋል። አሁንም በእናንተ እጅግ ስለሚታመን ከበፊት ይልቅ እጅግ ትጉህ ነው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ብዙ ጊዜ በብዙ መንገድ ተፈትኖ ትጉህ ሆኖ የተገኘውን ወንድማችንን ከነቲቶ ጋር የላክነውም በዚሁ ምክንያት ነው፤ እርሱ በእናንተ ላይ ያለው እምነት ትልቅ ስለ ሆነ አሁን በዚህ ሥራ ለመርዳት ያለው ትጋት ከምንጊዜውም የበለጠ ነው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ብዙ ጊዜም በብዙ ነገር መርምረን ትጉ እንደ ሆነ ያገኘነውን፥ አሁንም በእናንተ እጅግ ስለሚታመን ከፊት ይልቅ እጅግ ትጉ የሚሆነውን ወንድማችንን ከእነርሱ ጋር እንልካለን። Ver Capítulo |