አባቶቻችን ስደተኞች እንደ ነበሩ እኛ በፊትህ ስደተኞችና መጻተኞች ነን፤ ዘመናችንም በምድር ላይ እንደ ጥላ ናት፤ አትጸናምም።
2 ቆሮንቶስ 5:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ሁልጊዜ እመኑ፥ ጨክኑም፤ በዚህ ሥጋ ሳላችሁም እናንተ እንግዶች እንደ ሆናችሁ ታውቃላችሁ፤ ከሥጋችሁም ተለይታችሁ ወደ ጌታችን ትሄዳላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሁልጊዜ በመታመን እንኖራለን፤ በሥጋ እስካለን ድረስ ከጌታ ርቀን እንደምንገኝ እናውቃለን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ሁልጊዜ እንታመናለን፤ በሥጋ እስካለን ድረስ ከጌታ ርቀን እንደምንገኝ ብናውቅም፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምድራዊ ሰውነታችን እስካለንበት ጊዜ ድረስ ከጌታ የራቅን መሆናችንን ብናውቅም እንኳ ሁልጊዜ በእርሱ እንተማመናለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና በሥጋ ስናድር ከጌታ ተለይተን በስደት እንዳለን የምናውቅ ከሆንን፥ |
አባቶቻችን ስደተኞች እንደ ነበሩ እኛ በፊትህ ስደተኞችና መጻተኞች ነን፤ ዘመናችንም በምድር ላይ እንደ ጥላ ናት፤ አትጸናምም።
የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ “ብትጸጸትና ብታለቅስ ትድናለህ፤ የት እንዳለህም ታውቃለህ፤ በከንቱ ታምነሃልና፤ ኀይላችሁም ከንቱ ይሆናል፤ እናንተ ግን መስማትን እንቢ አላችሁ፤
ራፋስቂስም አላቸው፥ “ለሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፦ ታላቁ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ በማን ትተማመናለህ?
በምድር ያለው ማደሪያ ቤታችን ቢፈርስም፥ በሰማይ በእግዚአብሔር ዘንድ የሰው እጅ ያልሠራው ዘለዓለማዊ ቤት እንዳለን እናውቃለን።
እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፤ ተስፋቸውንም አላገኙም፤ ነገር ግን ከሩቅ አይተው እጅ ነሱኣት፤ በምድሪቱም ላይ እነርሱ እንግዶችና መጻተኞች እንደ ሆኑ ዐወቁ።
እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤
እኔ ወንድማችሁ የሆንሁ ከእናንተም ጋር አብሬ መከራውንና መንግሥቱን የኢየሱስ ክርስቶስንም ትዕግሥት የምካፈል ዮሐንስ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ምስክር ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ።