Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ቆሮንቶስ 5:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ስለዚህ ሁልጊዜ እንታመናለን፤ በሥጋ እስካለን ድረስ ከጌታ ርቀን እንደምንገኝ ብናውቅም፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ስለዚህ ሁልጊዜ በመታመን እንኖራለን፤ በሥጋ እስካለን ድረስ ከጌታ ርቀን እንደምንገኝ እናውቃለን፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በምድራዊ ሰውነታችን እስካለንበት ጊዜ ድረስ ከጌታ የራቅን መሆናችንን ብናውቅም እንኳ ሁልጊዜ በእርሱ እንተማመናለን።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እን​ግ​ዲህ ሁል​ጊዜ እመኑ፥ ጨክ​ኑም፤ በዚህ ሥጋ ሳላ​ች​ሁም እና​ንተ እን​ግ​ዶች እንደ ሆና​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ከሥ​ጋ​ች​ሁም ተለ​ይ​ታ​ችሁ ወደ ጌታ​ችን ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6-7 እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና በሥጋ ስናድር ከጌታ ተለይተን በስደት እንዳለን የምናውቅ ከሆንን፥

Ver Capítulo Copiar




2 ቆሮንቶስ 5:6
15 Referencias Cruzadas  

የምንኖርበት ምድራዊ ድንኳን የሆነው ሕይወት ቢፈርስ፥ በሰማይ ዘላለማዊ የሆነ በእጅ ያልተሠራ፥ በእግዚአብሔር የታነጸ መኖሪያ እንዳለን እናውቃለን።


እነዚህ ሁሉ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል ሳያገኙ እምነታቸውን እንደ ጠበቁ ሞቱ፤ ሆኖም ከርቀት አይተውት ሰላምታ አቀረቡለት፤ በዚህ ምድር ሲኖሩም እንግዶችና መጻተኞች ለመሆንም ታመኑ።


እኔ ዮሐንስ፥ ከእናንተ ጋር አብሬ በኢየሱስ መከራውንና መንግሥቱንና ጽናቱን የምካፈል ወንድማችሁ፥ በእግዚአብሔር ቃልና በኢየሱስ ምስክርነት ምክንያት ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ።


እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር አብሬ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ የሆንኩ፥ የክርስቶስም መከራ ምስክር የሆንኩ፥ እንዲሁም ወደ ፊት የሚገለጠው ክብር ተካፋይ የምሆን፥ በመካከላችሁ ያሉትን የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ።


ስለዚህ ታላቅ ዋጋ ያለውን መታመናችሁን አትጣሉ።


አዎ፥ ታምነናል፤ ይልቁንም ከሥጋ ተለይተን በጌታ ዘንድ መኖር እንመርጣለን።


ራፋስቂስም እንዲህ አላቸው፦ “ለሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፦ ታላቁ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ይህ የምትተማመንበት መተማመኛ ምንድነው?


የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ ኃይላችሁ በጸጥታና በመታመን ይሆናል፤ እናንተ ግን እምቢ አላችሁ፥


ጌታን ለሚፈራ ጠንካራ መታመን አለው፥ ለልጆቹም መጠጊያ ይኖራል።


እኔ በምድር እንግዳ ነኝ፥ ትእዛዛትህን ከእኔ አትሰውር።


በተግሣጽህ ስለ ኃጢአቱ ሰውን ዘለፍኸው፥ የሚመኘውንም እንደ ብል ታጠፋበታለህ፥ በእውነት ሰው ሁሉ ከንቱ ነው።


አባቶቻችንም ሁሉ እንደ ነበሩ እኛ በፊትህ እንግዶችና መጻተኞች ነን፤ ዘመናችንም በምድር ላይ እንደ ጥላ ነው፥ አይጸናም።


በዚህ ነዋሪ የሆነች ከተማ የለችንም፤ ነገር ግን ወደ ፊት የምትመጣዋን ከተማ እንፈልጋለን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios