2 ቆሮንቶስ 10:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፊታችሁ ያለውን ተመልከቱ፤ ማንም በክርስቶስ ያመነ ቢሆን፥ ይህን እንደ ገና በራሱ ይቍጠረው፤ እርሱ የክርስቶስ እንደ ሆነ እኛም እንዲሁ ነንና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ የምትመለከቱት ውጫዊውን ነገር ብቻ ነው። ማንም የክርስቶስ በመሆኑ ቢመካ እርሱ የክርስቶስ እንደ ሆነ ሁሉ እኛም የክርስቶስ መሆናችንን ሊገነዘብ ይገባዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፊታችሁ ያለውን ተመልከቱ። ማንም የክርስቶስ መሆኑን ተረድቶ ከሆነ፥ እርሱ የክርስቶስ እንደሆነ እኛም የክርስቶስ መሆናችንን እንዳይዘነጋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ የምትመለከቱት በውጪ የሚታየውን ነገር ብቻ ነው፤ ማንም ሰው የክርስቶስ ነኝ ብሎ ቢተማመን እንደገና ያስብበት፤ እኛም እንደ እርሱ የክርስቶስ መሆናችንን ይገንዘብ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፊታችሁ ያለውን ተመልከቱ። ማንም የክርስቶስ መሆኑን ተረድቶ ቢሆን፥ ይህን እንደ ገና በራሱ ይቁጠረው፤ እርሱ የክርስቶስ እንደ ሆነ እኛ ደግሞ እንዲሁ ነን። |
እርሱም፥ “እናንተስ ለሰው ይምሰል ትመጻደቃላችሁ፤ እግዚአብሔርም ልቡናችሁን ያውቃል፤ በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሔር ዘንድ የተናቀ ይሆናልና።
እነሆ፥ እርስ በርሳችሁ፥ “እኔ የጳውሎስ ነኝ፤ እኔ የአጵሎስ ነኝ፤ እኔ የኬፋ ነኝ፤ እኔ የክርስቶስ ነኝ” የምትሉትን እነግራችኋለሁ።
ራሱን እንደ ነቢይ አድርጎ ወይም መንፈስ ቅዱስ እንዳደረበት አድርጎ የሚቈጥር ቢኖር፥ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ነውና ይህን የጻፍሁላችሁን ይወቅ።
ነገር ግን ሰው ሁሉ በየሥርዐቱ ይነሣል፤ በመጀመሪያ ከሙታን የተነሣ ክርስቶስ ነው፤ ከዚያ በኋላ በክርስቶስ ያመኑ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ ይነሣሉ።
እኔ ነጻ አይደለሁምን? ሐዋርያስ አይደለሁምን? ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ያየሁ አይደለሁምን? እናንተስ በጌታችን ሥራዬ አይደላችሁምን?
ወንድሞቻችን ሆይ፥ እኔ ጳውሎስ በእናንተ ዘንድ ፊት ለፊት ሳለሁ ትሑት የሆንሁ፥ ከእናንተ ብርቅ ግን የምደፍራችሁ በክርስቶስ የዋህነትና ቸርነት እማልዳችኋለሁ፥ በፍቅራችሁ እታመናለሁና።
እነርሱ የክርስቶስ አገልጋዮች ቢሆኑም እኔም እንደ ሰነፍ ለራሴ እናገራለሁ፤ እኔ እበልጣለሁ፤ እጅግም ደከምሁ፤ ብዙ ጊዜ ተገረፍሁ፤ ብዙ ጊዜም ታሰርሁ፤ ብዙ ጊዜም ለሞት ተዘጋጀሁ።
ወደ እናንተ የመጣና እኛ ወደ አላስተማርናችሁ ወደ ሌላ ኢየሱስ የጠራችሁ ቢኖር፥ ወይም ያልተቀበላችሁት ሌላ መንፈስ ቢኖር፥ ወይም ያልተማራችሁት ሌላ ወንጌል ቢኖር ልትጠብቁን ይገባል።
እነሆ እናንተ ስላገበራችሁኝ በመመካቴ ሰነፍ ሆንሁ፤ ለእኔማ በእናንተ ዘንድ ልከብርና እናንተም ምስክሮች ልትሆኑኝ ይገባኝ ነበር፤ እኔ እንደ ኢምንት ብሆንም ዋናዎቹ ሐዋርያት ሁሉ ከሠሩት ሥራ ያጐደልሁባችሁ የለምና።
ክርስቶስ በእኔ አድሮ እንደሚናገር ማስረጃ ትሻላችሁና፤ እርሱም ሁሉ የሚቻለው ነው እንጂ፥ በእናንተ ዘንድ የሚሳነው የለም።
በዚህ ደግሞ በእናንተ ዘንድ ራሳችንን የምናመሰግን አይደለም፤ ነገር ግን እኛ እንደምንመካባችሁ፥ እናንተም በእኛ እንድትመኩ፥ ከልብ ሳይሆን ለሰው ይምሰል በሚመኩ ሰዎች ዘንድ መልስ እንዲሆናችሁ ምክንያትን እንሰጣችኋለን።
እኛ ከእግዚአብሔር ነን፤ እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል፤ ከእግዚአብሔር ያልሆነ አይሰማንም። የእውነትን መንፈስና የስሕተትን መንፈስ በዚህ እናውቃለን።
እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፥ “ፊቱን፥ የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንደሚያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” አለው።