Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ቆሮንቶስ 10:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እና​ን​ተን ለማ​ነጽ እንጂ፥ እና​ን​ተን ለማ​ፍ​ረስ ያይ​ደለ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ና​ንተ ላይ በሰ​ጠን ሥል​ጣን እጅግ የተ​መ​ካ​ሁት መመ​ካት ቢኖር አላ​ፍ​ርም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ጌታ በሰጠን ሥልጣን እጅግ ብመካም በዚህ አላፍርም፤ ሥልጣኑን የተቀበልነው እናንተን ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ አይደለምና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በሥልጣናችን ከበፊቱ ይልቅ አሁን ብመካም እንኳን፥ ይህን ጌታ የሰጠን እናንተን ለማነጽ እንጂ እናንተን ለማፍረስ ስላልሆነ አላፍርበትም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ጌታ ስለ ሰጠን ሥልጣን በጣም ብመካም አላፍርበትም፤ ይህ ሥልጣን የተሰጠን እናንተን ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ጌታ እናንተን ለማነጽ እንጂ እናንተን ለማፍረስ ያይደለ በሰጠው በሥልጣናችን ከፊት ይልቅ ብመካ እንኳ አላፍርም።

Ver Capítulo Copiar




2 ቆሮንቶስ 10:8
12 Referencias Cruzadas  

ደስ የሚ​ላ​ች​ሁን እን​ድ​ታ​ደ​ርጉ እን​ረ​ዳ​ች​ኋ​ለን እንጂ እን​ድ​ታ​ምኑ ግድ የም​ን​ላ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ በእ​ም​ነት ቆማ​ች​ኋ​ልና።


የጦር ዕቃ​ችን ሥጋዊ አይ​ደ​ለ​ምና፥ ጽኑ ምሽ​ግን በሚ​ያ​ፈ​ርስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ነው እንጂ።


ነገር ግን በመ​ል​እ​ክ​ቶች የማ​ስ​ፈ​ራ​ራ​ችሁ እን​ዳ​ይ​መ​ስ​ላ​ችሁ፥ ይህን ትም​ክ​ሕ​ቴን እተ​ወ​ዋ​ለሁ።


እኛስ ደግሞ ስለ ራሳ​ችን የም​ን​ከ​ራ​ከ​ራ​ችሁ ይመ​ስ​ላ​ች​ኋ​ልን? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በክ​ር​ስ​ቶስ ሆነን እን​ና​ገ​ራ​ለን፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ይህ ሁሉ ግን እና​ንተ ትታ​ነጹ ዘንድ ነው።


ልመካ ብሻም አላ​ዋቂ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ እው​ነ​ቱን እና​ገ​ራ​ለ​ሁና፤ ነገር ግን ስላ​ዩ​ኝና ስለ ሰሙኝ እን​ደ​ም​በ​ልጥ አድ​ር​ገው እን​ዳ​ይ​ጠ​ራ​ጠ​ሩኝ ትቸ​ዋ​ለሁ።


ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለማ​ፍ​ረስ ያይ​ደለ ለማ​ነጽ በሰ​ጠን ሥል​ጣን ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ ቍርጥ ነገር እን​ዳ​ላ​ደ​ር​ግ​ባ​ችሁ፥ ሥል​ጣን እን​ዳ​ለው ሰው ከእ​ና​ንተ ጋር ሳል​ኖር ይህን እጽ​ፋ​ለሁ።


ለዕ​ው​ነት ጸን​ተን እን​ኖ​ራ​ለን እንጂ፤ ከዕ​ው​ነት መው​ጣት አን​ች​ል​ምና።


ስለ እና​ንተ ለእ​ርሱ በተ​መ​ካ​ሁ​በት ሁሉ አላ​ሳ​ፈ​ራ​ች​ሁ​ኝ​ምና፤ ነገር ግን ሁሉን ለእ​ና​ንተ በእ​ው​ነት እንደ ተና​ገ​ርን፥ እን​ደ​ዚሁ ደግሞ በቲቶ ፊት ትም​ክ​ህ​ታ​ችን እው​ነት ሆነ።


በእ​ና​ንተ ዘንድ እን​ዲሁ ብዙ መወ​ደድ አለኝ፤ ስለ እና​ን​ተም የም​መ​ካ​በት ብዙ ነው፤ መጽ​ና​ና​ት​ንም አገ​ኘሁ፤ ከመ​ከ​ራ​ዬም ሁሉ ይልቅ ደስ​ታዬ በዛ​ልኝ።


በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስና ከሙ​ታን ለይቶ በአ​ስ​ነ​ሣው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ ነው እንጂ ከሰ​ዎች ወይም በሰው ሐዋ​ርያ ካል​ሆነ ከጳ​ው​ሎስ፥


ስለዚህም ምክንያት ይህን መከራ ደግሞ ተቀብዬአለሁ፤ ነገር ግን አላፍርበትም፤ ያመንሁትን አውቃለሁና፤ የሰጠሁትንም አደራ እስከዚያ ቀን ድረስ ሊጠብቅ እንዲችል ተረድቼአለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos