2 ዜና መዋዕል 9:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኪራም አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮችም ከሴፌር ለሰሎሞን ወርቅ አመጡ፤ የሰንደል እንጨትና የከበረ ዕንቍም ደግሞ አመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኪራም ሰዎችና የሰሎሞን ሰዎች ከኦፊር ወርቅ እንደዚሁም ሰንደልና የከበሩ ድንጋዮች አመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኦፊርም ወርቅ ያመጡ የኪራም ባርያዎችና የሰሎሞን ባርያዎች የሰንደል እንጨትና የከበረ ዕንቁ ደግሞ አመጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከኦፊር ወርቅ ያመጡ የንጉሥ ኪራምና የንጉሥ ሰሎሞን ሰዎች ከዚያው ከኦፊር የሰንደል እንጨትና ዕንቊ ለሰሎሞን አምጥተውለት ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከኦፊርም ወርቅ ያመጡ የኪራም ባሪያዎችና የሰሎሞን ባሪያዎች የሰንደል እንጨትና የከበረ ዕንቍ ደግሞ አመጡ። |
ለንጉሡም ከኪራም መርከቦች ጋር በባሕር ውስጥ የተርሴስ መርከቦች ነበሩት፤ በየሦስት ዓመትም አንድ መርከብ ከተርሴስ ወርቅና ብር፥ የተቀረጸና የተደረደረ ዕንቍ ይዞ ይመጣ ነበር።
ደግሞም አገልጋዮችህ ከሊባኖስ እንጨት መቍረጥ እንዲያውቁ እኔ አውቃለሁና ከሊባኖስ የዝግባና የጥድ፥ የሰንደልም እንጨት ላክልኝ።
ኪራምም መርከቦችንና የባሕርን ነገር የሚያውቁትን መርከበኞች በአገልጋዮቹ እጅ ላከለት፤ እነርሱም ከሰሎሞን አገልጋዮች ጋር ወደ ሴፌር መጡ፤ ከዚያም አራት መቶ አምሳ መክሊት ወርቅ ወስደው ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን አመጡ።
ንጉሡም ከሰንደሉ እንጨት ለእግዚአብሔር ቤትና ለንጉሡ ቤት ደርብ፥ ለመዘምራኑም መሰንቆና በገና አደረገ፤ እንደዚህም ያለ በይሁዳ ምድር ከቶ አልታየም ነበር።
ለንጉሡም መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ፥ እጅግም ብዙ ሽቱ፥ የከበረም ዕንቍ ሰጠችው፤ የሳባም ንግሥት ለንጉሡ ለሰሎሞን እንደ ሰጠችው ያለ ሽቱ ከቶ አልነበረም።