Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 9:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ንጉ​ሡም ከሰ​ን​ደሉ እን​ጨት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና ለን​ጉሡ ቤት ደርብ፥ ለመ​ዘ​ም​ራ​ኑም መሰ​ን​ቆና በገና አደ​ረገ፤ እን​ደ​ዚ​ህም ያለ በይ​ሁዳ ምድር ከቶ አል​ታ​የም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ንጉሡም የሰንደሉን ዕንጨት ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና ለቤተ መንግሥቱ ደረጃ መሥሪያ እንደዚሁም ለመዘምራኑ የመሰንቆና የበገና መሥሪያ አደረገው፤ ይህን የመሰለ ነገር በይሁዳ ምድር ከቶ አልታየም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ንጉሡም ከሰንደሉ እንጨት ለጌታ ቤትና ለንጉሡ ቤት እርከኖችን፥ ለመዘምራኑም መሰንቆና በገና ሠራ፤ እንደዚህም ያለ በይሁዳ ምድር ከቶ አልታየም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሰሎሞንም የሰንደሉን እንጨት የቤተ መቅደሱንና የቤተ መንግሥቱን ደረጃዎች እንዲሁም የመዘምራኑን መሰንቆና በገና አሠራበት፤ እነዚህን የዜማ መሣሪያዎች የመሰለ ከዚያ በፊት በይሁዳ ምድር ከቶ አልታየም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ንጉሡም ከሰንደሉ እንጨት ለእግዚአብሔር ቤትና ለንጉሡ ቤት ደርብ፥ ለመዘምራኑም መሰንቆና በገና አደረገ፤ እንደዚህም ያለ በይሁዳ ምድር ከቶ አልታየም ነበር።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 9:11
9 Referencias Cruzadas  

ንጉ​ሡም ከተ​ጠ​ረ​በው እን​ጨት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና ለን​ጉሡ ቤት መከታ፥ ለመ​ዘ​ም​ራ​ኑም መሰ​ን​ቆና በገና አደ​ረገ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በም​ድር ላይ እን​ደ​ዚያ ያለ የተ​ጠ​ረበ እን​ጨት ከቶ አል​መ​ጣም፤ በየ​ትም ቦታ አል​ታ​የም።


አራቱ ሺህም በረ​ኞች ነበሩ፤ አራቱ ሺህም ለም​ስ​ጋና በተ​ሠ​ሩት በዜማ ዕቃ​ዎች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ነበር።


ዳዊ​ትና የሠ​ራ​ዊቱ አለ​ቆ​ችም ከአ​ሳ​ፍና ከኤ​ማን ከኤ​ዶ​ት​ምም ልጆች በመ​ሰ​ን​ቆና በበ​ገና፥ በጸ​ና​ጽ​ልም የሚ​ዘ​ምሩ ሰዎ​ችን ለማ​ገ​ል​ገል ለዩ፤ በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውም ሥራ የሚ​ሠሩ ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።


ደግ​ሞም አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ከሊ​ባ​ኖስ እን​ጨት መቍ​ረጥ እን​ዲ​ያ​ውቁ እኔ አው​ቃ​ለ​ሁና ከሊ​ባ​ኖስ የዝ​ግ​ባና የጥድ፥ የሰ​ን​ደ​ልም እን​ጨት ላክ​ልኝ።


የኪ​ራም አገ​ል​ጋ​ዮ​ችና የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ከሴ​ፌር ለሰ​ሎ​ሞን ወርቅ አመጡ፤ የሰ​ን​ደል እን​ጨ​ትና የከ​በረ ዕን​ቍም ደግሞ አመጡ።


እር​ስ​ዋም ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን ካመ​ጣ​ችው የበ​ለጠ፥ ንጉሡ ሰሎ​ሞን የወ​ደ​ደ​ች​ውን ሁሉ፥ ከእ​ር​ሱም የለ​መ​ነ​ች​ውን ሁሉ ለሳባ ንግ​ሥት ሰጣት፤ እር​ስ​ዋም ተመ​ልሳ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችዋ ጋር ወደ ሀገ​ርዋ ሄደች።


መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፤ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos