የውስጠኛውንም አደባባይ ቅጥር ሦስቱን ተራ በተጠረበ ድንጋይ፥ አንዱንም ተራ በዝግባ ሣንቃ ሠራው፤ በመቅደሱ ፊት ለፊት ላለው ቤት ወለልም መጋረጃ ሠራ።
2 ዜና መዋዕል 4:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም የካህናቱን አደባባይ ፥ ታላቁንም አደባባይ፥ የአደባባዩንም ደጆች ሠራ፤ ደጆቻቸውንም በናስ ለበጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የካህናቱንም አደባባይ ሠራ፤ እንዲሁም ታላቁን አደባባይና በሮቹን ከሠራ በኋላ በናስ ለበጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም የካህናቱን አደባባይ፥ ታላቁንም አደባባይ፥ የአደባባዩንም ደጆች ሠራ፥ ደጆቻቸውንም በናስ ለበጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰሎሞን ለካህናቱ አገልግሎት የሚውለውን ውስጠኛ አደባባይ፥ እንዲሁም ታላቁን አደባባይ አሠራ፤ እንዲሁም በሁለቱ አደባባዮች መካከል የሚገኙትን በሮች አሠርቶ በነሐስ እንዲለበጡ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም የካህናቱን አደባባይ፥ ታላቁንም አደባባይ፥ የአደባባዩንም ደጆች ሠራ፤ ደጆቻቸውንም በናስ ለበጠ። |
የውስጠኛውንም አደባባይ ቅጥር ሦስቱን ተራ በተጠረበ ድንጋይ፥ አንዱንም ተራ በዝግባ ሣንቃ ሠራው፤ በመቅደሱ ፊት ለፊት ላለው ቤት ወለልም መጋረጃ ሠራ።
በታላቁም አደባባይ ዙሪያ የነበረው ቅጥር እንደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ውስጠኛው አደባባይ ቅጥርና እንደ ቤቱ ወለል ሦስቱ ወገን በተጠረበ ድንጋይ አንዱም ወገን በዝግባ ሳንቃ ተሠርቶ ነበር።
“ለድንኳኑም አደባባይ ሥራ፤ ከጥሩ በፍታ የተሠሩ የአደባባዩ መጋረጃዎችም በደቡብ በኩል ይሁኑ። የአንዱም ወገን ርዝመት መቶ ክንድ ይሁን፤