ዖዝያንም ተቈጣ፤ በመቅደስም የሚያጥንበት ጥና በእጁ ነበረ፤ ካህናቱንም በተቈጣ ጊዜ በካህናቱ ፊት በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በዕጣኑ መሠዊያ አጠገብ ሳለ በግንባሩ ላይ ለምጽ ታየ።
2 ዜና መዋዕል 26:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታላቁ ካህን ዓዛርያስ፥ ካህናቱም ሁሉ ተመለከቱት፤ እነሆም፥ በግንባሩ ላይ ለምጽ ነበረ፤ ፈጥነውም አባረሩት፤ እርሱም ደግሞ እግዝአብሔር ቀሥፎት ነበርና ይወጣ ዘንድ ቸኰለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሊቀ ካህናቱ ዓዛርያስና ሌሎቹ ካህናት ሁሉ በተመለከቱት ጊዜ፣ በግንባሩ ላይ ለምጽ እንደ ወጣበት አዩ። ስለዚህ አጣድፈው አስወጡት፤ በርግጥ እርሱም ራሱ ለመውጣት ቸኵሎ ነበር፤ እግዚአብሔር አስጨንቆታልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታላቁም ካህን ዓዛርያስ ካህናቱም ሁሉ ተመለከቱት፥ እነሆም፥ በግምባሩ ላይ ለምጽ ነበረ፤ ፈጥነውም እንዲወጣ አስገደዱት፥ እርሱም ደግሞ ጌታ ቀሥፎት ነበርና ለመውጣት ቸኮለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐዛርያስና ሌሎቹም ካህናት በታላቅ ድንጋጤ የንጉሡን ግንባር ትኲር ብለው ተመለከቱ፤ ከቤተ መቅደስም እንዲወጣ አስገደዱት፤ ዖዝያም እግዚአብሔር እንደ ቀጣው ዐውቆ ለመውጣት ተጣደፈ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታላቁም ካህን ዓዛርያስ ካህናቱም ሁሉ ተመለከቱት፤ እነሆም፥ በግምባሩ ላይ ለምጽ ነበረ፤ ፈጥነውም አባርረሩት፤ እርሱም ደግሞ እግዚአብሔር ቀሥፎት ነበርና ይወጣ ዘንድ ቸኮለ። |
ዖዝያንም ተቈጣ፤ በመቅደስም የሚያጥንበት ጥና በእጁ ነበረ፤ ካህናቱንም በተቈጣ ጊዜ በካህናቱ ፊት በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በዕጣኑ መሠዊያ አጠገብ ሳለ በግንባሩ ላይ ለምጽ ታየ።
ንጉሡም ዖዝያን እስኪሞት ድረስ ለምጻም ነበረ፤ ለምጻምም ሆኖ ከእግዚአብሔር ቤት ርቆአልና በተለየ ቤት ይቀመጥ ነበር፤ ልጁም ኢዮአታም በቤተ መንግሥቱ ሆኖ በምድሩ ሕዝብ ላይ ይፈርድ ነበር።
“ትወርሱአት ዘንድ እኔ ወደምሰጣችሁ ርስት ወደ ከነዓን ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ እኔም የለምጽ ደዌ ምልክት በርስታችሁ ምድር ቤቶች ባደረግሁ ጊዜ፥
እግዚአብሔር በክሳት፥ በንዳድም፥ በጥብሳትም፥ በትኵሳትም፥ በድርቅም፥ በዋግም፥ በአረማሞም ይመታሃል፤ እስክትጠፋም ድረስ ያሳድዱሃል።
እግዚአብሔር ልትድን በማትችልበት በክፉ ቍስል ጕልበትህንና ጭንህን ከእግርህ ጫማ እስከ አናትህ ድረስ ይመታሃል።