Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 26:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ንጉ​ሡም ዖዝ​ያን እስ​ኪ​ሞት ድረስ ለም​ጻም ነበረ፤ ለም​ጻ​ምም ሆኖ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ርቆ​አ​ልና በተ​ለየ ቤት ይቀ​መጥ ነበር፤ ልጁም ኢዮ​አ​ታም በቤተ መን​ግ​ሥቱ ሆኖ በም​ድሩ ሕዝብ ላይ ይፈ​ርድ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ንጉሥ ዖዝያን እስከሚሞትበትም ቀን ድረስ ለምጽ ነበረበት። ለምጻም በመሆኑም ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተወግዶ ነበርና በተለየ ቤት ተቀመጠ። በዚያ ጊዜ ቤተ መንግሥቱን በኀላፊነት የሚመራውና የአገሩንም ሕዝብ የሚያስተዳድረው የንጉሡ ልጅ ኢዮአታም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ንጉሡም ዖዝያን እስኪሞት ድረስ ለምጻም ነበረ፤ ለምጻምም ሆኖ ከጌታ ቤት ተነጥሎአልና በተለየ ቤት ይቀመጥ ነበር፤ ልጁም ኢዮአታም በንጉሡ ቤት ላይ ሆኖ በምድሩ ሕዝብ ላይ ይፈርድ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ንጉሥ ዖዝያ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ የቆዳው በሽታ አለቀቀውም፤ ይህም በመሆኑ በተለየ ቤት ኖረ፤ ከእግዚአብሔርም ቤት እንዲገለል ተደረገ፤ ልጁ ኢዮአታም የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ በመሆን የአገሪቱን ሕዝብ ያስተዳድር ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ንጉሡም ዖዝያን እስኪሞት ድረስ ለምጻም ነበረ፤ ለምጻምም ሆኖ ከእግዚአብሔር ቤት ተቍርጦአልና በተለየ ቤት ይቀመጥ ነበር፤ ልጁም ኢዮአታም በንጉሡ ቤት ላይ ሆኖ በምድሩ ሕዝብ ላይ ይፈርድ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 26:21
9 Referencias Cruzadas  

በከ​ተ​ማ​ዋም በር አራት ለም​ጻ​ሞች ሰዎች ነበሩ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “እስ​ክ​ን​ሞት ድረስ በዚህ ለምን እን​ቀ​መ​ጣ​ለን?


ታላቁ ካህን ዓዛ​ር​ያስ፥ ካህ​ና​ቱም ሁሉ ተመ​ለ​ከ​ቱት፤ እነ​ሆም፥ በግ​ን​ባሩ ላይ ለምጽ ነበረ፤ ፈጥ​ነ​ውም አባ​ረ​ሩት፤ እር​ሱም ደግሞ እግ​ዝ​አ​ብ​ሔር ቀሥ​ፎት ነበ​ርና ይወጣ ዘንድ ቸኰለ።


ኢዮ​አ​ታ​ምም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ አም​ስት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ ስድ​ስት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም የሳ​ዶቅ ልጅ ኢየ​ሩሳ ትባል ነበር።


ደዌው ባለ​በት ዘመን ሁሉ ርኩስ ይሆ​ናል፤ እርሱ ርኩስ ነው፤ ብቻ​ውን ይቀ​መ​ጣል፤ መኖ​ሪ​ያ​ውም ከሰ​ፈር በውጭ ይሆ​ናል።


የነ​ጻ​ውም ሰው ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ ጠጕ​ሩ​ንም ሁሉ ይላ​ጫል፤ በው​ኃም ይታ​ጠ​ባል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል። ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገ​ባል፤ ነገር ግን ከቤቱ በውጭ ሆኖ ሰባት ቀን ይቀ​መ​ጣል።


ማር​ያ​ምም ከሰ​ፈር ውጭ ሰባት ቀን ተለ​ይታ ተቀ​መ​ጠች፤ ማር​ያ​ምም እስ​ክ​ት​ነጻ ድረስ ሕዝቡ አል​ተ​ጓ​ዙም።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ ከሰ​ፈሩ አወ​ጡ​አ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እንደ ተና​ገ​ረው፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos